Skip to content
Advertisements

የሊቨርፑሉ ዲያን ሎቭረን የማንችስተር ዩናይትድ አጨዋወትን ተቸ

ቅዳሜ በምሳ ሰአት ጨዋታ ዩናይትድ ሊቨርፑልን ከማስተናገዱ ቀደም ብሎ የቀዮቹ ተከላካይ ክሮሺያዊው ዲያን ሎቭረን በጆሴ ሞሪንሆው ማንችስተር ዩናይትድ አጨዋወት ላይ ትችት አቅርቧል።

ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው እርስበርስ የሚጫወቱት ሁለቱ ባላንጣ ክለቦች ኦልድትራፎርድ ላይ የሚያደርጉት የቅዳሜው ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል።

ሁለቱ ቡድኖች አንፊልድ ላይ አድርገውት የነበረው የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ የጆሴው ቡድን ይዞት በገባው አጨዋወት ትችት ቀርበውበት እንደነበር ይታወሳል።

ሎቭረን የአንፊልዱን ጨዋታ በማስታወስ ዩናይትዶች በሜዳቸው የሚያደርጉትን ጨዋታ ምን አይነት አቀራረብ ይዘው ሊገቡ ይችሉ ይሆን ሲል ይጠይቃል።

“በእርግጠኝነት ጠንካራ ጨዋታ ይሆናል።ባለፈው ጨዋታ ወደ እኛ ሜዳ ሲመጡ በጥልቀት ተከላክለው ነበር።አሁን ደግሞ እንዴት እንደሚጫወቱ እንመለከታለን።

“በእርግጠኝነት ነጥቡን ይፈልጉታል።ለነሱ ምናልባት አንድ ነጥብ ሊበቃቸው ይችላል ለኛ ግን በቂያችን አይደለም።

“እዚህ የተገኘነውን ያለንን ለመስጠት ነው።የምንጫወተው ሁሌ እንደምንጫወተው በማጥቃት ነው።” በማለት ቡድናቸው ለማሸነፍ እንጂ ለአቻ ብሎ ወደ ሜዳ እንደማይገቡ አሳውቋል።

Advertisements
%d bloggers like this: