የአርሴናሉ ኮከብ መሱት ኦዚል ለክለቡ አርሴናል በመቶ ጎሎች ላይ መሳተፍ ችሏል

Image result for mesut ozil

 

ጽሁፍ ዝግጅት ፡- መንሀጁል ሀያቲ

ጀርመናዊው የኳስ ጥበበኛ መሱት ኦዚል ሳንሴሮ ላይ በአሮፖ ሊጉ ጨዋታ አርሴናል ኤሲ ሚላንን ሁለት ለ ምንም ባሸነፈበት ምሽት ሁለቱንም ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡

ኦዚል ሳንሴሮ ላይ ሁለት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበሉን ተከትሎ በመድፈኞቹ ማሊያ 100 ጎሎች ላይ መሳተፍ ችሏል፤ 37 ጎሎችን ሲያስቆጥር 63 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ ማቀበል ችሏል።

በአሮፖ ሊጉ ምሽት ሳንሴሮ ላይ ደምቆ ያመሸው ጀርመናዊዬ መሱት ኦዚል ባለፉት 4 ተከታታይ ጨዋታዋች ላይ ወጤት የራቀውን አርሴናልን እና ከምንጊዜምው በላይ ጫና ላይ ላሉት ፈረንሳያዊዬ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር በትንሹም ቢሆን እፎይታን መፍጠር ችሏል።

Advertisements