እገዛ/ አርሰን ዌንገር ከቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ አለቃ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ድጋፍ ማግኘታቸውን ገለጹ

Image result for arsene wenger and sir alex ferguson

ጽሁፍ ዝግጅት ፡- መንሀጁል ሀያቲ

የአርሴናሉ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር ከተለያዬ ቦታዋች ትችቶችን እያስተናገዱ ቢሆንም ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን የድጋፍ መልእክት እንደደረሳቸው ገለፁ።

ሰር አሌክስ ፈርጉሰን አርሴን ቬንገር አስቸጋሪ ጊዜ ላይ ባሉበት ስአት በማበረታታት ከጎናቸው ቆመዋል። የቀድሞው የማንችስተር ዬናይትዱ ሌጀንድ እና የቀድሞው አሰልጣኝ የነበሩት አሌክስ ፈርጉሰን በአሰልጣኝነት ዘመናቸዉ ተፎካካሪያቸው ለነበሩት እና አሁን በአርሴናል ቤት የአሰልጣኝነት ዘመናቸው እየጨለመባቸው ላሉት አርሴን ቬንገር የድጋፍ መልእክት ልከዋል።

በመድፈኞቹ ቤት በከባድ ጫና ውስጥ ያሉት አርሴን ቬንገር ስለ መልእክቱ ሲናገሩ ፦ ” ብዙ የፅሁፍ መልእክቶችን እቀበላለሁ በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ ፤ አሁን እና ድሮ ከፈርጉሰን ጋር ጥሩ ግንኙነት ነው ያለን. አንዳንዴ ነገሮች ጥሩ በማይሆኑልኝ ስአት የፅሁፍ መልእክቶች ይልክልኛል።”

“በእግር ኳስ ውስጥ እንደዚህ አይነት ችግሮች የማያጋጥሙበት እድል የለም, ያጋጥሙሀል ፤ ትልቁ ነገር ከዚህ ለመውጣት መፍትሄ መፈለጉ ላይ ነው።”

Advertisements