ሪከርድ / ሜሱት ኦዚል ኤሪክ ካንቶና ይዞት የነበረውን ሪከርድ ሰበረ

ጀርመናዊው የአርሰናል የአጥቂ አማካይ የሆነው ሜሱት ኦዚል መድፈኞቹ ዋትፎርድን ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ የቀድሞው የሊድስ እና የማንችስተር ዩናይትዱ አማካይ ኤሪክ ካንቶና ይዞት የነበረውን ሪከርድ ሰብሮታል።

ከአርሰናል ጋር የነበረው ቆይታ ውሉን በማራዘም ታማኝነቱን የገለፀው ኦዚል የቡድኑን የማጥቃት እንቅስቃሴ በማቀላጠፍ እየተጫወተው የሚገኘውን ሚና ቀጥሎበታል።

ተጫዋቹ ይበልጥኑ የሚታወቀው ጣጣቸውን የጨረሱ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ሲሆን መድፈኞቹ የሚያስቆጥራቸው ጎሎች ውስጥ የራሱን አሻራ ያሳረፈባቸው ጎሎች ተበራክተዋል።

በሳምንቱ አጋማሽ በዩሮፓ ሊግ ወደ ጣሊያን አቅንተው ተጠባቂውን ጨዋታ ኤሲ ሚላንን 2-0 ሲያሸንፉ ራምሴ ላስቆጠራት ጎል አመቻችቶ ማቀበሉ ይታወሳል።

ዋትፎርድን ባሸነፉበት በዛሬው የፕሪምየርሊግ ጨዋታም ለሽኮርዳን ሙስጣፊ አመቻችቶ በማሻማት የመጀመሪያው ጎል እንዲቆጠር እገዛ አድርጓል።

ኦዚል ለጎል አመቻችቶ ያቀበለው ኳስ በፕሪምየርሊጉ 50 ኛው ሆኖ የተመዘገበለት ሲሆን ይህም ኤሪክ ካንቶና ይዞት የነበረውን ሪከርድ እንዲሰብር አድርጎታል።

ኦዚል ሪከርዱን የሰበረው ብዙ ኳስ ለጎል እንዲሆኑ አመቻችቶ በማቀበል ሳይሆን 50 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በትንሽ ጨዋታ ላይ ማስመዝገብ በመቻሉ ነው።

የቀድሞው የሊድስ እና የማን ዩናይትዱ አማካይ ኤሪክ ካንቶና በ 143 ጨዋታዎች 50 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማመቻቸት ሪከርዱን ጨብጦ የነበረ ሲሆን ኦዚል በበኩሉ 50 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ማመቻቸት የቻለው 141 ጨዋታዎችን በማድረግ ብቻ ነው።

50 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በጥቂት የፕሪምየርሊግ ጨዋታዎች ማቀበል የቻሉ እስከ አምስት በዝርዝር

1) ሜሱት ኦዚል በ 141 ጨዋታዎች

2)ኤሪክ ካንቶና በ 143 ጨዋታዎች

3) ዴኒስ ቤርካምፕ በ 146 ጨዋታዎች

4) ሴስክ ፋብሪጋዝ በ 165 ጨዋታዎች

5) ዴቪድ ሲልቫ በ 166 ጨዋታዎች ናቸው።

ሴስክ ፋብሪጋዝ በፕሪምየርሉጉ 111 ጊዜ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማመቻቸት ቅድሚያውን ሲይዝ ዋይን ሩኒ እና ፍራንክ ላምፓርድ በ 102 እና በ 103 ኳሶች ይከተላሉ።

4) ዴኒስ ቤርካምፕ 94 ኳሶች

5) ስቴቨን ጄራርድ 92 ኳሶችን በማቀበል የፕሪምየርሊጉ ብዙ ለጎል የሚሆን በማቀበል እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

Advertisements