ኢዎቢ አርሰናሎች በወቅታዊ ብቃታቸው ላይ እንደሚነጋገሩ ገለፀ


የአርሰናሉ አማካኝ አሌክስ ኢዎቢ ኤሲሚላንን 2ለ0 መርታቱን ተከትሎ ክለቡ ከጨዋታዎች ውጤት በኋላ በወቅታዊ አቋሙ ላይ እንደሚነጋገርበት ገልፅዋል።

መድፈኞቹ በዩሮፓ ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታቸው ላይ ያገኙት ድል አርሰናል በእንግሊዝ እግርኳስ ሊግ ዋንጫ ፍፃሜ ላይ እና በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበላይ አራት ውስጥ ገብቶ ለማጠናቀቅ በሚደረገው ፉክክር ለደረሱበት ተከታታይ የሊግ ሽንፈቶች አዎንታዊ ምላሽ የሰጡበት ሆኗል።

ኢዎቢ አርሰናል እሁድ ከዋትፎርድ ጋር ከሚያደረግው ጨዋታ በፊት የክለቡ ተጫዋቾች መጥፎ ለነበሩት ውጤቶቻቸው የሰጡት ምላሽ ጥሩ “ምሳሌ” ሊሆን እንደሚችል ለጋዜጠኞች ተናገሯል።

“ተጫዋቾቹን አውቃቸዋለሁ። ቡድኑ ላይም ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው።” ሲል የ21 ዓመቱ ተጫዋች ተናግሮ “ነገሮች በመልካም ሁኔታ በማይጓዙባቸው ጊዜያት ሰዎች በመገናኛ ብዙኃኑ ላይ ብዙ ነገር እንደሚናገሩ ግልፅ ነው። ነገር ግን እኛ እርስ በእርስ እንነጋገራለን።

“ምናልባት ንግግራችን ሜዳ ላይ ጎልቶ ላይታይ ስለሚችል ያንን ላትመለከቱት ትችሉ ይሆናል። ነገር ግን እኛ ነገሮች እንደታቀዱት ሳይሆኑ ሲቀሩ እንነጋገርበታልን። በመከላከሉ እና በማጥቃቱ ላይ የተሻለ ነገር ማድረግ እንደምንችልም እናውቃለን።

“መሰረታዊው ነገር በአንድ ላይ የምንከላከልበትን እና የምናጠቃበትን መንገድ መፈለጉ ላይ ነው። በዚያ ላይም መስራት ይኖርብናል። ያንንም እናውቃለን። ያንን ለማድረግም ጥረት እያደረግን እንገኛለን። በቅርቡም የዚያን ዓይነቱን የአንድነት ምልክት ማሳየት እንችላለን።” በማለት ጨምሮ ተናግሯል።

አርሰናል በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በአምስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ቼልሲዎች በ11 ነጥቦች ዝቅ ብሎ በስድተኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ዛሬ [እሁድ] ሆርኔቶችን የመጥም ይሆናል።

Advertisements