​”ማቲች ለእኔ ትክክለኛው ተጨዋች ነው ” – ጆዜ ሞሪንሆ 

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ኒማኒያ ማቲችን ለማንችስተር ዬናይትድ ትክክለኛው ፈራሚ በማለት አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

በመንሃጁል ሃያቲ

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከቸልሲ ማንችስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ሰርቢያዊ አማካኝ ኒማኒያ ማቲች በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ድንቅ የሆነ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል።

ማንችስተር ዬናይትድ ሊቨርፑልን በሜዳው ባስተናገደበት ጨዋታ ላይ ከወጣቱ የማንችስተር አካዳሚ ውጤት ከሆነው ማክቶሚናይ ጋር በመሰለፍ የዬናይትድን የመሀል ሜዳ በአግባቡ መምራት የቻለ ሲሆን ፣ በኦልድ ትራፎርድ እያሳየ ላለው ምርጥ አቋም ከአሰልጣኙ አድናቆት ተችሮታል። 
አሰልጣኙ ከሊቨርፑሉ ድል በሆላ ስለ ማቲች የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል ፦

“ኒማኒያ ማቲች ከእኔ እና ከማንችስተር ዬናይትድ ጋር መስራት እንደሚፈልግ ስሰማ ፤ ለእኔ ትክክለኛው ተጨዋች ነው ነበር ያልኩት።”

“ያን ያልኩት ተጨዋቹ ባለው የተጨዋችነት ጥራት ብቻ ሳይሆን በሁለታችን መካከል ባለው ግንኙነትም ነው፤ እኔ በድምብ አውቀዋለው እሱም እንደዛው.”

የ29 አመቱ ሰርቢያዊ ከሞሪንሆ ጋር በቸልሲ ቤት አብረው እንደሰሩ የሚታወስ ሲሆን፤ ምንም እንኳን ማቲች ዬናይትድ ከተቀላቀለ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም በደጋፊው ፣ በአሰልጣኙና በቡድን ጓደኞቹ ተወዳጅነት ማግኘት የቻለ ተጨዋች ነው።

Advertisements