“ሰኞ ቀን ስጫወት መጥፎ እድል ነው ያለኝ ” – ፔፕ ጓርዲዬላ

Image result for pep guardiola

ጽሁፍ ዝግጅት መንሀጁል ሀያቲ

ሰኞ ምሽት ከሜዳቸው ውጭ ስቶክ ሲቲን የሚገጥሙት የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዬላ ቡድኑ በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ ላይ ሲጫወት እንደማያስደስተው አስተያየቱን ሰጥቷል።

ጋርዲዬላ በሰጠው አስተያየትም ፦ ” ሰኞ ቀን ስጫወት መጥፎ እድል ነው ያለኝ ፤ ከሜዳክ ውጭ ከስቶክ ጋር ስትጫት ከባድ ነው በፕሪሚየር ሊጉ ለመቆየት ስለሚጫወቱ ከባድ ጨዋታ ነው የሚሆነው.” ® “ባለፈው የውድድር ዘመን ወደ ስቶክ ተጉዘን ማሸነፋችን እድለኞች ነን፤ በሊጕ ለመቆየት ከሚጫወቱ ቡድኖች ጋር ስትጫወት ከባድ ነው።”

“ሰኞ ምሽት መጫወት አልወድም ምክንያቱም በሁለቱ የሳምንቱ የእረፍት ቀናት ሁሉም ይዝናናል፤ የእረፍቱ ቀናት ሲጠናቀቁ፤ ሳምንቱ ያለቀ ይመስልሀል ጨዋታዋች እንደሌሉ ይሰማሀል ነገር ግን መጫወት አለብህ።” ጋርዲዬላ  ፔፕ ሰኞ ቀን በባርሳ በነበረበት ወቅት ጥሩ ነገር እንዳልገጠመው ተናግሯል፡፡

ሲቲዋች በሰኞ ምሽቶች በሊጉ በኤቨርተን ፤ ከኤፍ ኤ ካፑ ደግሞ በዊጋን ተሸንፈው ከውድድሩ ውጭ እንደሆኑ የሚታወስ ነው። የፕሪሚየር ሊጉ መሪ የሆኑት ማንችስተር ሲቲዋች ሰኞ ምሽት ከሜዳቸው ውጭ ከስቶክ ሲቲ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ በማሸነፍ መሪነታቸውን በማጠናከር ወደ ዋንጫው በጣም የሚጠጉበትን እድል ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Advertisements