“ሳረጅ ደሀ ሆኜ የአለም ዋንጫን በትዝታ እያሰብኩ መኖር አልፈልግም” – ኦስካር

ወደ ቻይና ያቀናው የቀድሞ የቼልሲ አማካይ የነበረው ብራዚላዊው ኦስካር በአለም ዋንጫ ላይ የመሳተፍ እድሉ የጠበበ ሲሆን ተጫዋቹም በአለም ዋንጫ ላይ ቢሳተፍም ባይሳተፍም ግድ እንደማይሰጠው ነገርግን ወደ ቻይና ማቅናቱ ሲያረጅ ደሀ መሆን ስለማይፈልግ እንደሆነ አሳውቋል።

ኦስካር ወደ ቻይና ያደረገው ዝውውር ብዙዎቹን ያስገረመ ነበረ።በወጣትነት እድሜው ይህን አይነት ውሳኔ እንደሚወስን ሳይጠበቅ 2016 ላይ ወደ ቻይና አቅንቷል።

ተጫዋቹ በቻይና ቆይታ አድርጎ ለብሄራዊ ቡድኑ ጥሪ ይደረግለታል ተብሎ ስለማይታሰብ በ 2018 የአለም ዋንጫ ላይ የሀገሩን ማሊያ ለብሶ የመጫወት እድሉ ጠባብ ሆኗል።

ይህን የተረዳው ኦስካር በአለም ዋንጫ ላይ ባይሳተፍ ግድ እንደማይሰጠው በመናገር ወደ ቻይና ያደረገው ዝውውር በራሱ አስተያየት ትክክል እንደሆነ አሳውቋል።

“ለአለም ዋንጫ ላይ ባልሳተፍ ግድ አይሰጠኝም።ትችት መቅረብ ያለበት ወደ ቻይና በማቅናቴ ነው።እኔ ግን በግሌ ስለ ቤተሰቤ እና ስለ ራሴ የወደፊት ሁኔታ አስባለው።ሳረጅም ደሀ ሆኜ የአለም ዋንጫን በትዝታ እያሰብኩ መኖር አልፈልግም።” ሲል ተናግሯል።

ኦስካር ለቻይናው ሻንጋይ ኤስ አይ ፒ ጂ 60 ሚ ፓውንድ በሆነ በኤሽያ የዝውውር ሪከርድ ከፈረመ በኋላ አሁንም ከክለቡ ጋር ቆይታ እያደረገ ይገኛል።

ተጫዋቹ በቅርቡም የነ ኒኮላስ ጋይታን  እና ካራስኮ ቡድን የሆነው ዳሊያን ይፋንግን 8-0 ሲያሸንፉ ሀትሪክ መስራቱ ይታወሳል።

Advertisements