በዳኛው ውሳኔ የተበሳጩት የግሪኩ የክለብ ባለቤት ሽጉጥ ታጥቀው ወደሜዳ ገቡ

የግሪኩ ክለብ ፓኦክ ባለቤት የሆኑት ሳቪዲስ ክለባቸው እሁድ ዕለት በአንድ የግሪክ ወሳኝ ጨዋታ ላይ በመጫወት ላይ ሳለ በዳኛው ውሳኔ ብስጭት ገብቷቸው መሳሪያ እንደታጠቁ ያለፈቀድ ወደሜዳ በመግባት ውዝግብ ፈጥረዋል

ድረጊቱ የተከሰተው በግሪኩ ሱፐርሊግ በቀንደኛ ተቀናቃኞቹ ፓኦክ እና ኤኢኬ አቴንስ መካከል እየተደረገ በነበረው ጨዋታ የፓኦኩ ተከላካይ ፈርናንዶ ቫሬላ በመጨረሻ ሰዓት ላይ ያስቆጠራትን ግብ ዳኛው አለማፅደቃቸውን ተከትሎ ነበር።

ግቡ መፅደቅ አለመፅደቁ እያወዛገበ በነበረበት አጋጣሚም ሳቪዲስ በወገባቸው ላይ ሽጉጣቸውን እንደታጠቁ በግል ጠባቂዎቻቸው ታጅበው በብስጭት ወደሜዳው በመግባት ለያዥ ለገራዥ ሲያስቸግሩም ታይተዋል። የሳቪዲስ ድርጊትን ተከትሎም ጨዋታው እንዲቋረጥ ሆኗል።

“ወዲያውኑ ሻምፒዮንሺፑ እንዲቋረጥ ውሳኔ ላይ ደርሰናል።” ሲሉ የግሪክ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስቴር የሆኑት ጂዮርጊዮስ ቫሲሊያዲስ በጉዳዩ ላይ ከሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር አሌክሲስ ቲስፓሪስ ጋር ተወያይተው ከተነጋግሩ በኋላ ኢአርቲ ለተሰኘው የግሪክ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

“ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ጋር እየተነጋገርንበት የምንገኝ ሲሆን፣ ግልፅ በሆነ እና ሁሉንም በሚያስማማ መንገድ ስምምነት ላይ እስክንደርስ ድረስ ሻምፒዮንሺፑ እንዲቀጥል አናደርግም። በመሆኑም ህጉን እና ደንቡን ተግባራዊ እናደርገለን። ለተሻለ እግርኳስ እና ተጠያቂነትም መታገላችን እንቀጥላለን።” ሲሉ ምክትል ሚኒስቴሩ ጨምረው ተናግረዋል።

ቫሲላዲስ ይህን ንግግር ከመናገራቸው በፊት ለሲኤንኤን ስፓርት የቴሌቭዥን ጣቢያ “የታጠቁ ባለስልጣናት ወደእግርኳስ ሜዳ በመግባት ወደኋላ ብዙ ዓመታትን የኋልዮሽ እንድንጓዝ የሚያደርግ ትዕይንት ፈጥረዋል። ይህ ዓይነቱ ድርጊት ጠንከር ያለ ውሳኔ ሊተላለፍበት ይገባል።

“ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ጋር ጠንከር ያለ ውሳኔ ማሳለፍ የሚኖርብን ቢሆንም እንኳ ማንም ሰው ከዒላማችንን ውልፍት እንዲያደረግን አንፈቅድለትም።” ሲሉም ተናግረው ነበር።

የዓለም አቀፉ የእግርኳስ አመራር አካል ፊፋ ጉዳዩን አስመልክቶ ይህን ዓይነቱን ባህሪ ፈፅሞ እንደሚንኮንን ገልፃ “አጋጣሚው በሃገር ውስጥ ውድድር ላይ እንደመፈጠሩ የስነምግባር ቅጣት ውሳኔዎቹ በሙሉ በግሪክ እግርኳስ ማህበር የሚዳኙ መሆናቸውንም” አሳውቋል።

የድርጊቱ መንስኤ የሆኑት የፓኦክ ክለብ ባለቤት ሳቪዲስ ምንም እንኳ የታጠቁት መሳሪያ ህጋዊ ቢሆንም ያለፈቃድ ወደሜዳ በመግባታቸው ግን የእስር ትዕዛዝ የተለለፈባቸው መሆኑ ተዘግቧል።

ይሁን እንጂ “ኢቫን (ሳቪዲስ)ማንም ሰው በመሳሪያ አላስፈራሩም።” ሲል የክለቡ የሚዲያ ክፍል ለሩሲያው ስፓርት ኤክስፕሬስ ጋዜጣ ገልፅዋል።

“ይህ ማለት በአንዳድን የመገናኛ ብዙኃን ላይ የወጣው የተጋነነ ርዕሰ ጉዳይ ፈፅሞ ውሸት ነው። እሱ የታጠቀው መሳሪያ በህግ የተፈቀደለትን ነው። ይህ ደግሞ በግሪክ የሚፈቀድ ነገር ነው።” ሲል የሚዲያ ክፍሉ ለጋዜጣው አክሎ ተናግሯል።

“ኢቫን ሳቪዲስ ክለቡን ለመከላከል እና በስራአስፈፃሚዎቹ እና ረዳቶቻቸው ላይ ለደሩባቸው ጥቃት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እየተዘገጁ ነው።” ሲል ክለቡ በድረገፁ ላይ በፅሁፍ የሳፈረው መግለጫ አመልክቷል።

ሳቪዲስ ከዚህ ቀደም ከ2007 እስከ 2011 ባለው ጊዜ በሩሲያው መንግስት በዱማ ግዛት የምክትልነት ስልጣን የነበራቸው የግሪክና የሩሲያ ዝርያ ያላቸው የቢዝነስ ሰው እና ፓለቲከኛ ናቸው።

Advertisements