ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሲቪያ | የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ማንችስተር ዩናይትድ ከ2014 ወዲህ በሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜን ለመጀመሪያ ጊዜ የመቀላቀል ውጥን ይዞ 16 ክለቦች በቀሩት የማክሰኞ ምሽቱ የመልስ ጨዋታ ሲቪያን በኦልድትራፎርድ ይገጥማል።

ቀያይ ሰይጣኖቹ ምስጋና ለግብ ጠባቂያቸው ዴቪድ ደኽያ ይሁንና በኢስታዲዮ ራሞን ሳንቼዝ ፒዢዋን ከሲቪያ ጋር ባደረጉት በመጀመሪያው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ 0ለ0 በሆነ ውጤት መለያየት ችለዋል። ዩናይትዶች በዚህ ጨዋታ በማጥቃቱ ሚና ላይ መልካም እንቅስቃሴ ባያሳዩም በጨዋታው ላይ 25 የግብ ሙከራዎችን ያዳረጉትን የሲቪያዎችን ጥቃት ግን መመከት ችለው ነበር።

የክለቦቹ ወቅታዊ አቋም


ዩናይትድ ከሲቪያ ጋር ካደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ አንስቶ በተከታታይ ያደረጋቸውን ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ከመቻላቸውም በላይ ባለፉት ሳምንታት የሊጉ የበላይ አራት ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚፎካከሯቸውን ቀንደኛ ተቀናቃኞቻቸውን ቼልሲን እና ሊቨርፑልን ማሸነፍም ችለዋል።

በሌላ በኩል የስፔኑ ክለብ ሲቪያ ወቅታዊ ውጤቶች ግን የተደበላለቁ ነበሩ። ከዩናይትድ ጋር በአቻ ውጤት ካጠናቀቁ ወዲህ ባደረጉት ጨዋታ በአትሌቲኮ ማድሪድ 5ለ2 ሲሸነፉ፣ በተከታታይ ደግሞ ማላጋን እና አትሌቲክ ቢልባዎን ማሸነፍ ችለዋል። ነገር ግን ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጉትን ጨዋታ በቫሌንሺያ መሸነፋቸው በላ ሊጋው አራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ክለብ በ11 ነጥቦች ርቀው እንዲቀመጡ ተገደዋል።

የክለቦቹ ዜናዎች


በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ሊቨርፑልን ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ በታፋ ጉዳት ምክኒያት ያልተሰለፈው ፓል ፖግባ በዚህ ጨዋታ ላይ መሰለፉ አጠራጣሪ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ጉዳት አንደር ሄሬራም በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ተጫዋች ነው።

ሌላው ፈረንሳያዊ ተጫዋች አንቶኒ ማርሻል በዚህ ጨዋታ ላይ መሰለፉ አጠራጣሪ የሆነ ተጫዋች ሲሆን ሌሎች በጉዳት ላይ የሚገኙትን እና በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፉትን ፊል ጆንስን፣ ዴሊ ብሊንድን፣ እና ማርኮስ ሮሆን ሊቀላቀልም ይችላል።

በአንፃሩ ሲቪያ ኼሱስ ናቫስ በማክሰኞ ምሽቱ ጨዋታ ላይ እንደማይሰለፍ በይፋ ገልፀዋል። ሰባስቲያን ኮርቺያ በብሽሽት ጉዳት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ሌላኛው ተጫዋች ነው። እንዲሁም ከፓርቶ በውሰት ያመጡት ሚጉዌል ላዩን በፓርቱጋሉ ክለብ በዚህ ውድድር ላይ ተስልፎ በመጫወቱ ለዚህ ጨዋታ ብቁ ያልሆነ ተጫዋች ነው።

ግምታዊ አሰላለፎች


ማንችስተር ዩናይትድ (4-2-3-1)

ደ ኽያ- ቫሌንሺያ፣ ስሞሊንግ፣ ቤሊ፣ ያንግ፣ – ፓግባ፣ ማቲች፣ ራሽፎርድ፣ ማታ፣ ሳንቼዝ – ሉካኩ

አሰልጣኝ: ኾዜ ሞሪንሆ

ሲቪያ (4-2-3-1)

ሪኮ – ሜርካዶ፣ ክያር፣ ሌንግሌት፣ ኢስኩዴሮ፣ ን’ዞንዚ፣ ባኔጋ፣ ሳራቢያ፣ ቫስኩዌዝ፣ ኮሬያ፣ ሙሪየል

አሰልጣኝ: ቪንቼንዞ ሞንቴላ

የክለቦቹ የእርስበርስ ግንኙነት አኃዛዊ መረጃ


  • ዩናይትድ ከስፔን ክለቦች ጋር ለመጨረሻንጊዜ በሜዳው ላይ ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ብቻ ነው።
  • ዩናይትዶች ከሜዳቸው ውጪ በመጀመሪያው ጨዋታ ካደረጓቸው 15 ጨዋታዎች 11 ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችለዋል።
  • ዩናይትዶች በ16ቱ የሻምፒዬንስ ሊግ ዙር ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች ማለፍ የቻሉት በአንዱ ብቻ ነው።
  • ሲቪያ በሻምፒዮንስ ሊጉ ፈፅሞ ወደሩብ ፍፃሜ አልፎ አየውቅም።
  • ሲቪያ በእንግሊዝ ምንን አይነት ጨዋታ አሸንፎ አያውቅም (አቻ 3፣ ሽን 3)።
  • የስፔኑ ክለብ ከአውሮፓ መድረኮች ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጋቸው 11 ጨዋታዎች በሁለቱ ብቻ ሽንፈት ደርሶበታል።
Advertisements