አንቶኒዮ ኮንቴ ከመሲ ጋር የተነጋገሩት ምንድ ነው?

የቼልሲው አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ ረቡዕ ምሽት በሻምፒዮንስ ሊጉ በኑ ካምፕ በባርሴሎና ከደረሰባሰባቸው ሽንፈት በኋላ ሊዮኔል መሲን በወዳጅነት አቅፈው እያናገሩት ሜዳውን ለቀው ሲወጡ ታይተዋል።

ሰማያዊዎቹ በስፔኑ ክለብ በደርሶ መልስ 4ለ1 በሆነ አጠቃላይ ውጤት ተሸንፈው በሻምፒዮንስ ሊጉ የነበራቸው ጉዞም ተገቷል።

በምሽቱ ጨዋታ አርጄንቲናዊው ኮከብ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር በሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ ያስቆጠራቸውን ግቦች 100 ማድረስ ችሏል።

ሰማያዊዎቹ በሊዮኔል መሲ ሶስት የደርሶመልስ ጨዋታ ግቦች ተሸንፈው ከውድድሩ ውጪ ይሁኑ አንጂ ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ግን አሁንም በክለባቸው ላይ ከፍ ያለ የመንሳሳት ስሜት አላቸው።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም የአምስት ጊዜ የባሎን ዶሩን አሸናፊ የፊት ተጫዋች ቀርበውና በእቅፋቸው ውስጥ በማስገባት እንኳን ደስ አለህ ብለውታል። አፋቸውን ሸፍነውም እየተነጋገሩ ወደመልበሻ ክፍል ገብተዋል።

አንቶኒዮ ኮንቴ ከጨዋታው በኋላ ከመሲ ጋር ስለተነጋገሩት ነገር ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦለቸውም ነበር።

“ከመሲ ጋር ትልቅ የሆነ ደስታህን የምትገልፅበት ዕድል ስታገኝ ደስታህን የምትገልፅበት ትክክለኛው ዕድል ይህ ይመስለኛል።

“ጫፍ የደረሰ እና በአንድ የውድድር ዘመን ላይ ብቻ ሳይሆን በየውድድር ዘመኑ ሁሉ 60 ግቦችን ማስቆጠር የሚችል ልዕለ ኃያል የሆነን ተጫዋች የምታወድስበት ትክክለኛው ጊዜም ይኸው ነው።

“ከጨዋታው በኋላም ደስታዬን ለእሱ ለመግለፅ ዕድሉን በማግኘቴ ደሰኛ ነኝ። ምክኒያቱም የምናወራው ስለዓለማችን ምርጥና እጅግ ድንቅ ስለሆነ ተጫዋች ነው።” ሲሉ ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ተናግረዋል።

ቼልሲዎች በመጪው የሳምንቱ መጨረሻ በኤፍኤ ዋንጫው ሌስተርን ከመግጠማቸሙ በፊት ከደረሰባቸው ሽንፈት በቶሎ ማገገም ይኖርባቸዋል። ምክኒያቱም ውድድሩ ሰማያዊዎቹ የዋንጫ ጆሮ ሊጨብጡ የሚችሉበት ብቸኛ ውድድር ነው።

Advertisements