“ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ”- የወቅቱ ተፈላጊ አሰልጣኝ!

ቶተንሀምን ከታላላቆች ቡድኖች ውስጥ ተፎካካሪ እንዲሆን ያደረጉት ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በሌሎች ቡድኖች እየታደኑ ያሉ የወቅቱ ተፈላጊ አሰልጣኝ ሆነዋል።

ስፐርሶች ባለፉት ጥቂት አመታት በፕሪምየርሊጉም ይሁን በቻምፕየንስ ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው እየተወዳደሩ ይገኛሉ።

ለዚህ ደግሞ ስማቸው በጉልህ የሚነሳው የክለቡ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ሲሆን አሰልጣኙ እንደ ቡድንም ይሁን ተጫዋቾችን በግላቸው አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ እየሰሩ ያሉት ስራ እየተወደሰላቸው ይገኛል።

ምንም እንኳን ቡድኑ በዘንድሮው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊጉ ወደ ሩብ ፍፃሜ ባያልፉም በምድብ ጨዋታዎች ጨምሮ ከታላላቅ ቡድኖች ጋር ሲገናኙ እያደረጉ የሚገኙት ፉክክር ቡድኑ ለመሻሻሉ ምልክት ነው።

ይህን የተመለከቱ የአውሮፓ ሀያል ቡድኖች ማውሪሲዮ ፖቸቲኖን ለመቅጠር ፍላጎት በማሳደራቸው አሰልጣኙ የወቅቱ ተፈላጊ አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።

ከዚዳን ጋር መቆየታቸው እርግጥ ያልሆኑት ማድሪዶች እንዲሁም በአውሮፓ መድረክ ውጤታማ ያልሆኑት ፒ ኤስ ጂዎች አሰልጣኛቸውን የሚያሰናብቱ ከሆነ በመጀመሪያ የሚመለከቱት እኝሁ አሰልጣኝ ላይ እንደሚሆን እየተነገረ ይገኛል።

የጀርመኑ ባየርሙኒክም እንዲሁ የአሰልጣኙ ፈላጊ በመሆን ግኑኝነት እስከመፍጠር እንደደረሰ ተነግሯል።

ዮፕ ሄንክስን በአመቱ መጨረሻ ላይ እንደሚያጣ የሚገመተው ሙኒክ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖን ለማስፈረም ግንኙነት መፍጠሩን የቀድሞ ተጫዋች ዲትማር ሀማን ተናግሯል።

Advertisements