ሰበር ዜና፡ የሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የዕጣ ድልድል ይፋ ሆነ

የ2017/18 የውድድር ዘመን የሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች የዕጣ ድልድል በአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዋና መስሪያ ቤት መቀመጫ በሆነችው የስዊዘርላንዷ ከተማ ኒዮን ዛሬ (አርብ) ይፋ ሆኗል።

ወደሩብ ፍፃሜው ማለፋቸውን ያረጋገጡት ባርሴሎና (ስፔን)፣ ባየር ሙኒክ (ጀርመን)፣ ጁቬንቱስ (ጣሊያን)፣ ሊቨርፑል (እንግሊዝ)፣ ማንችስተር ሲቲ (እንግሊዝ)፣ ሪያል ማድሪድ (ስፔን፣ ወቅታዊው ሻምፒዮን)፣ ሮማ (ጣሊያን)፣ ሲቪያ (ስፔን) ነበሩ።

የሻምፒዮንስ ሊጉ የፍፃሜ አምባሳደር በነበረው የቀድሞው ዩክሬናዊ ተጫዋች አንድሬ ሼቪቼንኮ አስተባባሪነት በተከናወነው የዕጣ ድልድል የማውጣት ስነስርዓት እንደሚከተለው ሆኖ ወጥቷል።

በዚሁ ድልድል መሰረት የመጀመሪያ የሩብ ፋፃሜ ጨዋታዎች ማክሰኞ መጋቢት 25 እና ረቡዕ መጋቢት 26 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎቹ ማክሰኞ ሚያዝያ 2 እና ረቡዕ ሚያዝያ 3 የሚደረጉ ሲሆን በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የተቀመጡ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሜዳቸው ያደረጋሉ።

Advertisements