ሰበር ዜና፡ የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የዕጣ ድልድል ይፋ ሆነ

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የዕጣ ድልድልን ተከትሎ በስዊዘርላንድ ኒዮን በወጣው የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የዕጣ ድልድል ተፋላሚዎች ይፋ ሆነዋል።

በሩብ ፍፃሜ ለዕጣ ድልድል መብቃታቸውን ያረጋገጡት አትሌቲኮ ማድሪድ፣ አርቢ ሌፕዢግ፣ ላዚዮ፣ ስፖርቲንግ ሊስበን፣ ማርሴ፣ ሳልዝበርግ እና ሲኤስኬኤ ሞስኮው ናቸው።

እዚህ ዙር ላይ መድረስ የቻሉ ክለቦች ስምንት የተለያዩ ሃገራት ክለቦች ሲሆኑ፣ አንዳቸውም ባለፈው የውድድር ዘመን እዚህ ዙር ላይ ተሳተፊ አልነበሩም።

የዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱን ባስተባበረው ፈረንሳያዊው የቀድሞው የባርሴሎና ተጫዋች ኤሪክ አቢዳል አማካኝነት ድልድሉ እንደሚከተለው ሆኖ ወጥቷል።

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎቹም የመጀመሪያው ሃሙስ መጋቢት 6 እና የመልሱ ጨዋታ ሚያዝያ 4፣ 2010 ዓ.ም የሚደረጉ ይሆናል። በመጀመሪየው ረድፍ ላይ የተቀመጡ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሜዳቸው የሚያደርጉም ይሆናል።

Advertisements