ካርቫኻል ኔይማርን ማስፈረም ምርጫው ነው

የሪያል ማድሪዱ ተከላካይ ዳኒ ካርቫኻል የማስፈረም ምርጫ ቢሰጠው ከአንቱዋን ግሪዝማን ይልቅ ኔይማርን ማስፈረም እንደሚመርጥ ገልፅዋል።

ኔይማር የዓለም የዝውውር ክብረወሰን በሆነ ዋጋ ከባርሴሎና ወደፒኤስጂ የተዛወረው በቅርቡ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በአስገራሚ ሁኔታ ከላ ሊጋው ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ዝውውር ጋር ስሙ ተያይዟል።

ከኔይማር እና ከአትሌቲኮ ማድሪዱ ኮከብ ግሪዝማን ማንን እንደሚመርጥ ጥያቄ የቀረበት ካርቫኻልን ከብራዚላዊው ጋር ያለው በተቃራኒነት የመጫወት ተመክሮ እሱን እንዲመርጥ እንዳደረገው ተናገሯል።

“አስቸጋሪ…እንዳደረሰብኝ ስቃይ ከሆነ ግን ኔይማርን አስፈርማለሁ።” ሲል ካርቫኻል ለስፔኑ ሚዲያ ኤል ትራንዚስተር ተናግሯል።

ሪያል ማድሪድ የኔይማርን ክለብ ፒኤስጂን 5ለ2 በሆነ ከደርሶ መልስ ድምር ውጤት ከሻምፒዮንስ ሊጉ 16ቱ የጥሎ ማለፍ ዙር ውጪ አድርጎታል።

ካርቫኻል ማድሪድ ከዋነኛ ተቀናቃኙ እና ከላ ሊጋው መሪ ባርሴሎና በ15 ነጥቦች ዝቅ ብሎ በሚገኝበት የዚህ የውድድር ዘመን በሻምፒዮንስ ሊጉ ላይ እያሳከው ስለሚገኘው የስኬት ፋይዳም ይናገራል።

“በእጅጉ ጠቃሚ ነበር። ገና በመጋቢት ወር አጋማሽ ከሊጉ ውድድር ውጪ መሆናችን ለእኛ በእጅጉ መጥፎ ነበር።” ሲል ተናግሯል።

“200 ፐርሰንት [ፒኤስጂዎችን] እንደምናሸንፋቸው እናውቀው ነበር። የሆነውም ይኸው ነበር።” ሲልም አክሎ ተናግሯል።

Advertisements