የሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የዕጣ ድልድል

የዕጣ ድልድሉ መቼ ይወጣል?


የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ድልድል የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የስዊዘርላንድ ከተማ በሆነችው ኒዮን ዛሬ [አርብ] ከቀትር በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።

በዕጣ ድልድሉ ላይ እነማን ተካተዋል?


ባርሴሎና (ስፔን)
ባየር ሙኒክ (ጀርመን)
ጁቬንቱስ (ጣሊያን)
ሊቨርፑል (እንግሊዝ)
ማንችስተር ሲቲ (እንግሊዝ)
ሪያል ማድሪድ (ስፔን፣ ወቅታዊው ሻምፒዮን)
ሮማ (ጣሊያን)
ሲቪያ (ስፔን)

የማይገናኙ ክለቦች ይኖራሉ?


የሉም። የዚህኛው ዙር የዕጣ ማውጣት ድልድል ነፃ ሲሆን የትኛውንም ሃገር ክለብ ከየትኛውም ሃገር ክለብ ጋር (በአንድ ሃገር ላይ የሚገኙ ክለቦችን ቢሆኑም እንኳ) እርስ በርስ ሊያገናኝ ይችላል። የመጀመሪያው ዕጣ የወጣለት ክለብ የመጀመሪያውን ጨዋታ በሜዳው የሚያደርግ ይሆናል።

በዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱ ላይ ማን ይገኛል?


የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የሻምፒዮንስ ሊጉ የፍፃሜ አምባሳደር የሆነው አንድሬ ሼቪቼንኮ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱን የሚያስተባብር ይሆናል።

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎቹ መቼ ይደረጋሉ?


የመጀመሪያ ጨዋታዎች ማክሰኞ መጋቢት 25 እና ረቡዕ መጋቢት 26 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎቹ ማክሰኞ ሚያዝያ 2 እና ረቡዕ ሚያዝያ 3 የሚደረጉ ሲሆን፣ ትክክለኛ የጨዋታ መርሃግብሮቹ ደግሞ ከዕጣ ድልድሉ በኋላ ይፋ ይሆናሉ።

Advertisements