“ማንም ሰው ከእኔ ጋር አይነፃፀርም።” – ክርስቲያኖ ሮናልዶ

የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከእሱ “ክህሎት” ወይም “ተነሳሽነት” ጋር የሚፎካከሩ ብዙም ባለመኖራቸው ማንም ሰው ከእሱ ጋር “እንደማይነፃፀር” ያምናል።

ሮናልዶ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ማንችስተር ዩናይትድን በ2003 ተቀላቅሎ በአሌክስ ፈርጉሰን ስር መሻሻል በማሳየት ከዓለማችን ምርጥ ተጫዋቾች መካከል አንዱ መሆን ችሏል።

ሮናልዶ በ2008 የመጀመሪያ የባሎን ዶር ሽልማትን በዩናይትድ እያለ ያገኘ ቢሆንም፣ ያለጥርጥር ግን በእግርኳስ ህይወቱ ምርጡን ጊዜ ማሳለፍ የቻለው ለክለቡ ትልቅ አሻራን ማሳረፍ በቻለበት ሪያል ማድሪድ ነበር።

ከሊዮን መሲ ጋር ያለው የቆየ ፉክክርም በተለይም ወደላ ሊጋው ከመጣበት ጊዜ አንስቶ በብዙዎች ዘንድ አብይ የመከራከሪያ ጉዳይ ከሆነ ረጅም ጊዜ ሆኖታል።

ምንም እንኳ ብዙዎች የባርሴሎናው ተቀናቃኙ የበልጠ በተፈጥሮ የተሰጠ ብቃት እንዳለው ቢገልፁም፣ ነገር ግን የዚያኑ ያህል የሮናልዶን ተነሳሽነትና የስራ ትጋት የሚጠራጠሩ ጥቂቶች ናቸው።

ለአዲሱ የናይክ ማስታወቂያ ሲባል በይፋዊ የኢንስታግራም ገፁ ላይ የተናገረውን የለጠፈው ሮናልዶ “በመጀመሪያ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች የመሆን ህልም ነበረኝ።

“ጓደኞቼም “ምንድን ነው የምታወራው?’ እንደማለት ብለው ይመለከቱኛል። እጫወት የነበረው ለመዝናናት ለቀልድ ነበር። ነገር ግን በበአዕምሮዬ ያ ብቃቴ የጀመረው በማንችስተር ነበር። ያን ጊዜም ነበር ያን ማመን የጀመርኩት።

“የእኔ ዓይነት ክህሎት፣ ተነሳሽነት፣ ስራ፣ ስነምግርባር እና የእኔ አይነት እግርኳስ ያላቸውን ሰዎችን አልመለከትም። ማንም ሰው ከእኔ ጋር አይነፃፀርም። ማንም ሰው ክርስቲያኖ ሮናልዶን አይሆንም። አንተ የምትሆነው ራስህን ነው። እኔ ደግሞ ራሴን።” በማለት ተናግሯል።

Advertisements