የሆዜ ሞሪንሆ አስገራሚ ጋዜጣዊ መግለጫ

የስንብት ስጋት ውስጥ የሚገኙት የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ ቅዳሜ ምሽት በኤፍኤ ዋንጫ ብራይተንን 2ለ0 በመርታት ወደግማሽ ፍፃሜው ማለፍ ከቻሉበት ጨዋታ በፊት ዘለግ ያለ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል

ክለቡ ማክሰኞ ምሽት በሻምፒዮንስ ሊጉ በሲቪያ ተሸንፎ መውጣቱን ተከትሎ ፓርቱጋላዊው አሰልጣኝ የሚከተለውን 12 ደቂቃዎች የፈጀ አስገራሚ ንግግር ተናግረዋል።

ጋዜጠኛ

“በዚህ ሳምንት ከተወሰኑ ደጋፊዎች ጋር ተነጋግሬ ነበር። እነሱ ከሲቪያ ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ በታየው ብቃት ተበሳጭተዋል። ለእነዚህ ደጋፊዎች ምን የሚሉት ነገር አለ?”

ሞሪንሆ

“ለደጋፊዎች የምለው ደጋፊዎች ደጋፊዎች ናቸው። እናም ደጋፊዎች የራሳቸውን አስትያየት እና የራሳቸውን ሃሳብ የመስጠት መብት አላቸው።

“ነገር ግን ስለእግርኳስ ውርስ የምለው አለኝ። ከፍፅምና ያልፀዳ ቢሆንም በእኔ እንግሊዘኛ ፍፁም በሆነ መንገድ ከእኔው ፓርተጋልኛ [ቋንቋም] ለመተርጎም ጥረት አደርጋለሁ።

“ነገር ግን ቃል በቃል ትርጉም እንደእግርኳስ ውርስ ነው። እናም አንድ አሰልጣኝ የሚወርሰው ማንችስተር ዩናይትድ ብዙ ጊዜ ያልሆነውን ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፈውን የሻምፒዮንስ ሊግ ድል ነው፤ እሱም በ2008 የሆነ። የመጨረሻው የፍፃሜ ጨዋታው ደግሞ በ2011 ነበር።

“ከ2011፣ 2012 አንስቶ ከምድብ ማጣሪያ ውጪ ሆኗል። ምድቡም አሁን በዚህ የውድድር ዘመን ከነበርንበት ምድብ ጋር ከፍ ያለ ተመሳሳይነት ነበረው። ቤኔፊካ፣ ባሰል እና የሮማኒያው ጋላቲ። ነገር ግን ከምድብ ማጣሪያው ውጪ ነበር።

“በ2013 በኦልትራፎርድ ከመጨረሻዎቹ ከ16ቱ ዙር ውጪ ሆኑ። በወቅቱ እኔም በሌላ የተቀያሪ ወንበር ላይ አገኝ ነበር (በሪያል ማድሪድ በአሰልጠኝነት)

“በ2014 ከሩብ ፍፃሜው ውጪ ሆነ።

“በ2015 ምንም ዓይነት የአውሮፓ እግርኳስ ተሳትፎ አልነበረውም።

“በ2016 ወደአውሮፓ እግርኳስ ተሳትፎ ተመለሰ። ከዚያም ከምድብ ማጣሪው ውጪ ሆነ እና ወደዩሮፓ ሊጉ በመግባት በሁለተኛው ጥሎ ማለፍ ከዩሮፓ ሊግም ወጣ።

“በ2017 በዩሮፓ ሊጉ ላይ ተጫወተ እና በእኔ አማካኝነት የዩሮፓ ሊጉ ሻምፒዮን በመሆን ወደሻምፒዮንስ ሊጉ ተመለሰ።

“በ2018 የምድብ በማጣሪያው ማግኘት ከሚገባን 18 ነጥብ በ15 ነጥቦችን በማሳካት አለፍን። ከዚያም በ16ቱ ማጣሪያ በሜዳችን ተሸነፍን።

“ስለዚህ በሰባት ዓመታት ውስጥ አራት የተለያዩ አሰልጣኞች ቢኖሩትም አንድ ጊዜ ለአውሮፓ ውድድር አላለፈም፤ ሁለት ጊዜ ከምድብ ማጣሪያው ውጪ ሆነ፤ የተሻለው አንድ ጊዜ ለሩብ ፍፃሜ የበቃበት ነው።

“ወደፕሪሚየር ሊጉ ለማምራት ከፈለግክ ደግሞ ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፈው በ12-13 (የውድድር ዘመን) ነበር። እናም በአራት ተከታታይ የውድድር ዘመኖች ዩናይትድ የጠናቀቀው አምስተኛ፣ ስድስተኛ እና ሰባተኛ ወይም ሰባተኛ፣ አራተኛ ፣ አምስተኛ እና ስድስተኛ በመሆን ነበር።

“ስለዚህ ባለፉት የመጨረሻ አራት ዓመታት ምርጥ የነበረው ደረጃ አራተኛ ነበር። ይህ ነው እንግዲህ የእግርኳስ ውርስ።

“ይህም ማለት ሂደቱን ስትጀምር የምትገኘው እዚህ ወይም እዚያ ነው። ውርስ ማለት ይኸው ነው።

“እናም ደጋፊዎቹን ሁልጊዜም አከብራለሁ። አንተ ለነጋገርከቸው በርካታዎቹ ደጋፊዎችም ሆነ፣ እኔም ላነጋገርኳቸው በርካታ ደጋፊዎች እኔ በጣም ዕድለኛ ነኝ ወይም በጣም ዕድለኛ አይይደለሁም።

“ነገር ግን አንተ ያነጋገርካቸው በጣም ተበሳጭተዋል። ነገር ግን እኔ ያነጋገርኳቸው ግን የእግርኳስን ውርስ የሚያውቁ ናቸው።

“ሂደቱን ምን እንደሆነም ሆነ መቼ እንደሚደርሱ የሚያውቁ ናቸው።

“ሪያል ማድሪድ እንደደረስኩ ምን ያህሉ ተጫዋቾች በሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ ላይ መጫወት ችለው እንደነበር ታውቃለህ?

“ዣቢ አሎንሶ ከሊቨርፑል ጋር፣ ኢከር ከሲያስ ከሪያል ማድሪድ ጋር እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሪያል ማድሪድ ጋር።

“የተቀሩት በሙሉ ሩብ ፍፃሜን እንኳ አያውቁትም። ይህ ነው እንግዲህ የእግርኳስ ውርስ ማለት።”

ጋዜጠኛ

“ሆዜ እነዚያ አሃዞች…”

ሞሪንሆ

“እውነተኛ ናቸው። ሌላ እውነተኛ (አሃዝ) ትፈልጋለህ? ሌሎች ተጨማሪ እውነተኛ (አሃዞችን) እሰጥሃለሁ።

“ባለፉት ሰባት ዓመታቶች ውስጥ የማንችስተር ሲቲ የፕሪሚየር ሊጉ መጥፎ የሚባል ደረጃ አራተኝነት ነበር።

“ባለፉት ሰባት ዓመታቶች ውስጥ ማንችስተር ሲቲ ለሁለት ጊዜያት ያህል ሻምፒዮን ነበር። ከፈልግክም ለሶስተኛ ጊዜ ማለትም ትችላለህ። ምክኒያቱም ከአንድ፣ ከሁለት፣ ከሶስት ወይም ከአራት (ሳምንታት) በኋላ ሻምፒዮን ይሆናሉ። ይህ ነው ውርስ ማለት።

“ውርስ ማለትስ ሌላ ምን ማለት እንደሆነ ታውቃለህ?

“ኦታሜንዲ፣ ኬቨን ደ ብሩይኔ፣ ፈርናንዲንሆ፣ (ዴቪድ) ሲልቫ፣ ራሂም ስተርሊንግ፣ (ሰርጂዮ) አጉዌሮ ባለፉት ሁለት ሰምንታት ሳይሆን በቀደሙት ጊዜያት መዋዕለ ነዋይ ፈሰስ የተደረገባቸው ናቸው። ከዚያ ቀደም ባሉት ጊዜያት።

“ባለፈው የውድድር ዘመን ምን ያህል የዩናይትድ ተጫዋቾች ክለቡን እንደለቀቁ ታውቃለህ? የት እንደሚጫወቱም ተመልከት። የት ነው የሚጫወቱት እንዴትስ ነው የሚጫወቱት፣ እሱም እየተጫወቱ ከሆነ ነው። ይህ ነው እንግዲህ የእግርኳስ ውርስ።

“እናም እኔ አንድ ቀን ክለቡን ስለቅ ቀጣዩ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ እዚህ የሚያገኘው (ሮሜሉ) ሉካኩ፣ (ኒማኒያ) ማቲች ያለጥርጥርም ከበርካታ አመታት በፊት የነበረውን(ዴቪድ) ደ ኽያን ይሆናል። የሚያገኘው በርካታ አስተሳሰብ፣ የተለያዩ ብቃቶች፣ የተለያዩ መሰራታዊ ማንነት፣ የተለያዩ ደረጃዎች እና እውቀት ያላቸውን ተጫዋችንም ይሆናል።

“እናም በአንዳንድ ምክኒያቶች ልክ እንደዛሬው ለሻምፒዮንስ ሊጉ ሩብ ፍፃሜ ልትበቃ ትችላለህ፣ ያኔ ሁልጊዜም በዚያ ደረጃ ላይ የሚኖሩትን አራት ክለቦችን ታገኛለህ።

“ባርሴሎና ባልፉት ሰባትና ስምንት ዓመታት በዚያ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሪያል ማድሪድም ባለፉት ሰባት እና ስምንት ዓመታት በዚያ ደረጃ ላይ ደርሷል።

“ጁቬንትስም ሁልጊዜም አለ፤ ባየር ሙኒክም ሁልጊዜም አለ። እናም ያለጥርጥር አንደእኔው ኢንተር ሚላን ያለ ክለብም ይኖራል። ባለፈው ዓመት እንደነበረው ሞናኮም ሌላ ክለብ ይኖራል።

“ሁልጊዜም በዚያ ደረጃ ላይ የሚገኙ አንዳንድ ክለቦች በአንዳንድ ምክኒያቶች ሊገኙ ይችላሉ። ለዚያም አንዳንዳ ምክኒያት ይኖራል።

“እናም ለእኔ መልካሙ ነገር እና አስደናቂው ስሜት እንደባለቤቶቹ፣ እንደ (ምክትል ስራ አስፈፃሚው) (ኢድ) ዉድዋርድ፣ እንደ (አስተዳደራዊ ኃላፊው) (ሪቻርድ) አርኖልድ ሁሉ እኔም በትክክለኛው የጋራ አሰሳሰብ ላይ የምገኝ መሆኔ ነው። የሁላችንም የጋራ አስተሳሰብ በሚገባ ተመሳሳይ ነው።

“እኛ በሁሉም ነገር ላይ እንስማማለን። በሂደት ላይ እንደምንገኝም እናውቃለን። ፈሰስ በምናደርግባቸው መዋዕለ ንዋዮቻችንም ላይ እንስማማለን። ፈሰስ የምናደርግባቸው መዋዕለንዋዮቻችንም በየውድድር ዘመኑ እየተሻሻሉ ነው።

“ከመዋዕለ ንዋዮቻችንም በላይ የሆና ነገር ያስፈልገናል። ጊዜም ያስፈልገናል። የጋራ የሆነው ሃሳብችን በሙሉም ተመሳሳይ ነው።

“ስለዚህ (በዩናይትድ) ህይወት ጥሩ ነው።

“የምሰራው አስደናቂ ስራም አለኝ። ትናንት ከእኔ ስራ ጋር በቀጥታ ከማይገናኝ ነገር ግን በባርከታ መስኮች ላይ በክለባችን እየሰራ ከሚገኝ አንድ አዲስ ሰው ጋር ተገናኝቼ ነበር። ነገር ግን እሱ ከሌላ ክለብ የመጣ ሰው ነው። እንዲህ ሲልም ጠየቀኝ “ለምን ወደዚህ ለመምጣት ውሳኔ ላይ ደረስክ?”

“እናም ግለሰቡ “ምክኒያቱም እኔ በሌላ ክለብ ውስጥ አስደናቂ ስራ ሰርቻለሁ። በዚህ ክለብ ውስጥም ትልቅ ስራ እንዳለኝ፣ ትልቅ ስራም ከፊቴ እንደሚጠብቀኝ አውቃለሁ። ስለዚህ ወደዚህ የመጣሁት ለአንዳች ተግዳሮት ነው።’ ሲል ነገረኝ።

“ጥሩ አድርጓል። እኔም ወደዚህ ለመምጣት የወሰንኩት ለተመሳሳይ አላማ ነበር።

“ዕድሉን ባገኘሁበት እና የውድድር ዘመኑ ከመጀመሩ በፊት አሸናፊ ልሆን የምችልበት ሌላ ሃገር ሊግ ላይ ላሰለጥን እችል ነበር። ያን ማድረግ እችል ነበር። (ነገር ግን) አላደረግኩትም። የምገኘው እዚህ ነው።

“የምገኘው እዚህ ነው። በዚህም እቆያለሁ። አስተሳሰቤን የምቀይርበትም ምንም አይነት መንገድ የለም።

“ለእኔ አነተ አገላለፄን ስለማወቅህ አላውቅም። ለእንግሊዝ ያለው ትርጓሜ እንዲገባህ ማድረጉንም አላውቅም። ነገር ግን ‘ሁሉም ግድግዳ በር ነው።’ የሚል የምወደው አባባል አለ።

“ሁሉም ግድግዳ በር እንደሆነ ታውቃለህ?

“ለማንኛውም እኔ ሸሽቼ አልሄድም። ጨርሶም አልጠፋም። አላነባምም። ምክኒያቱም የሰማሁት ጥቂት የተቃውሞ ድምፅ ነው።

“በጥድፊያ ወደመልበሻ ክፍል መተላለፊያ በመሮጥም አልሰወርም።

“በቀጣዩ ጨዋታ ቀድሜ የምወጣው እኔ ነኝ። ደጋፊዎቹን አከብራለሁ። ምንም የምፈራው ነገር የለም። ተጠያቂነትም አያስፈራኝም።

“የ20 ዓመት ልጅ ሳለሁ በእግርኳስ ላይ ተራ ሰው ነበርኩ። የአንድ ተራ ሰው ልጅ ነበርኩ።

“በወቅቱ የነበረኝም ከፍ ያለ ኩራት ነበር። የ20 ዓመት ልጅ ሳለሁ የአንድ ተራ ሰው ልጅ ነበርኩ። ታውቃለህ?

“አሁን ግን በ55 ዓመቴ የአሁኑን ማንነቴን ይዣለሁ። በስራ ምክኒያት፣ በችሎታዬ ምክኒያት እና በአስተሳሰቤ ምክኒያት ያደረግኩትን አድርጌያለሁ።

“ስለዚህ በጋራ መሆን ይችላሉ። ይህንንም ከበርካታ በርካታ በርካታ በርካታ ከበርካታ ዓመታት በፊት ተረድቼው ነበር። እኔን ለማይወዱ ሰዎች ግን ይህ ነገር በእጅጉ አስቸገሪ ነበር።

“‘ይኸው በድጋሚ መጣ”፤ ‘ይኸው በድጋሚ አሸነፈ’፤ (እየተባልኩ ነው) ለ10 ወራት ግን ምንም አላሸነፍኩም።

“ለ10 ወራት ምንም አላሸነፍኩም። ለመጨረሻው ጊዜ ያነሳሁት ዋንጫ ከ10 ወራት በፊት ነበር። ታውቃለህ?

“ሊቨርፑልን አሸነፍኩ። ቼልሲን አሸነፍኩ። በሲቪያ ደግሞ ተሸነፍኩ። እናም አሁን ደስተኛ ልሆን የምችልበት ጊዜ ነው።

“ጥሩ። ጠላቶችህ ቢሆኑ እንኳ በሌሎች ደስታ ተደሰት ከሚለው ኃይማኖታዊ አቋም ትምህርትም ወስጃለሁ።

“ስለዚህ ባለህ አቋም እርጋ። እኔ በጣም ዕድለኛ ሰው ነኝ። እናም በማንነቴ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ።”

Advertisements