ፍጥጫ / የኤፍኤ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ድልድል ይፋ ሆነ

የእንግሊዝ ታሪካዊ ዋንጫ የሆነው የኤፍኤ ዋንጫ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ድልድል ይፋ ሆኗል።

በውድድሩ ግማሽ ፍፃሜ ማንችስተር ዩናይትድ ከቶትነሀም ሲገናኝ የስታምፎርድ ብሪጁ ቼልሲ ከሳውዝአምፕተን ይጫወታል። 

ስፐርስ ተጋጣሚው የነበረውን ስዋንሲን በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን ሲቀላቀል የጆሴ ሞውሪንሆው ዩናይትድ ደግሞ ብራይተንን 2-0 በማሸነፍ ከሰሜን ለንደኑ ቶትነሀም ተገናኝቷል። 

ቼልሲ በበኩሉ ቀበሮዎቹን ሌስተሮች በጭማሪ ሰዓት በመርታት በግማሽ ፍፃሜው ዊጋንን ከውድድሩ ካሰናበተው ሳውዝአምፕተን ጋር የሚፋጠጥበትን ውጤት አስመዝግቧል።  

የግማሽ ፍፃሜው ትንቅንቅ በመጪው ሚያዚያ አጋማሽ ባሉ ሁለት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል። 

Advertisements