ቆይታ / ሉክ ሾው በጆሴ ሞውሪንሆ ተደጋጋሚ ትችት ቢደርስበትም ከዩናይትድ እንዲለቅ ጫና እንደማይደረግበት ተገለፀ

ሉክ ሾው አሰልጣኝ ጆሴ ሞውሪንሆ እሱን በማስመልከት በአደባባይ በሚናገሯቸው ንግግሮች ደስተኛ ባይሆንም በመጪው ክረምት ከፍላጎቱ ውጪ ማንችስተር ዩናይትድን እንዲለቅ እንደማይገደድ ተገለፀ፡፡ 

እንግሊዛዊው ተመላላሽ በዩናይትድ ቀጣይ ቆይታው ዙሪያ ገና የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ባደርስም የውል ስምምነቱ በ 2019 ሲጠናቀቅ ከክለቡ መልቀቅን በመምረጥ በኦልትራፎርድ መቆየትን ሊመርጥ ይችላል።

ሾው የውል ስምምነቱ እስኪጠናቀቅ በዩናይትድ መቆየትን ምርጫው ካደረገ በትልቅ የደሞዝ የውል ስምምነት በነፃ ወደተለያዩ ክለቦች የማምራት እድል ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሞውሪንሆ በኤፍኤ ዋንጫው ሩብ ፍፃሜ ቡድናቸው ብራይተንን 2-0 በረታበት ጨዋታ ሾውን ለመጀመሪያው ግብ መቆጠር ምክንያት ቢሆንም በእረፍት ሰዓት ቀይረው አስወጥተውታል።

ፖርቹጋላዊው አወዛጋቢም የብራይተን ተጫዋቾች በእሱ በኩል ይዘውት የሚመጡት ኳስ አደጋ እንደሚፈጥር በማሰባቸውን እንደቀየሩትም ከጨዋታው በኋላ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በግልፅ ተናግረዋል፡፡

Advertisements