ተግሳፅ / አንድሬ ክርስቲንሰን ከአቋሙ መውረድ ጋር በተያያዘ የቀድሞው የቡድኑ ዝነኛ ተከላካይ ጆን ቴሪ የሰጠውን ምክር ይፋ አደረገ

 ​

የቼልሲው አንድሬ ክሪስቲንሰን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አቋሙ ከመውረዱ ጋር በተያያዘ የቀድሞውን ዝነኛ ተከላካይ እና የቡድን አጋሩን ጆን ቴሪን ማማከሩን ገለፆ ቴሪ የሰጠውን ምክር ይፋ አድርጓል፡፡ 

ዴንማርካዊው ኮከብ ለሁለት ዓመታት በጀርመኑ ቦሩሲያ ሞንቹድግላድባ የውሰት ቆይታን አድርጎ ወደቼልሲ ከተመለሰ ወዲህ በስታምፎርድ ብሪጉ ክለብ አስደናቂ አቋም በማሳየት የቋሚ ተሰላፊነትን አግኝቶ እንደነበር አይረሳም፡፡

ክሪስቲንሰን በሰማያዊዎቹ ቤት ዴቪድ ሊውዝን ከቋሚ አሰላለፍ ውጪ እስከማድረግ የዘለቀ ትልቅ እንቅስቃሴን ማድረግ ቢችልም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚሰራቸው ተደጋጋሚ ስህተቶች ልምድ አልባ መሆኑን እያሳበቁበት ይገኛል፡፡ 

የ 21 ዓመቱ ተከላካይ ከቴሪ ጋር የነበረውን ምክክር ሲያስረዳም የቀድሞው የሰማያዊዎቹ አምበል ስህተት ተፈጥሯዊ ነገር መሆኑን እንደነገረውና ዋናው ነገር በቀጣይ ስህተቶቹን መቅረፍ ላይ ማተኮር መሆኑን በመግለፅ ምክር እንደሰጠው ይፋ አድርጓል፡፡

ክርስቲንሰን የተቀበለውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ባሳበቀ መልኩም ሰሞነኛ ስህተቶቹን በመቅረፍ ቡድኑ በኤፍኤ ዋንጫ ስድስተኛ ዙር ሌስተር ሲቲን 2-1  በረታበትና ግማሽ ፍፃሜውን በተቀላቀለበት ጨዋታ አስደናቂ ብቃት ማሳየት ችሏል፡፡

Advertisements