አውባምያንግ የእረፍት ጊዜውን በምን እያሳለፈ ነው?

ፒየር-ኤመሪክ አውባምያንግ ከፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ርቆ በሚገኝበት በዚህ የአረፍት ወቅቱ ሁሉንም ህመሞቹን እና የህመም ስሜቶቹን ለመፈወስ አማራጭ የህክምና ዘዴ በሆነው ኦስቲዮፓት ህክምና ራሱን እየተንከባከበ ይገኛል።

ጋቦናዊው ተጫዋች የክለቡ የዝውውር ክብረወሰን በሆነ 56 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ መድፈኞቹን ከተቀላቀለበት ወርሃ ጥር አንስቶ ለክለቡ በስድስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

አርሰናል እስከመጋቢት 23፣ 2010 ዓ.ም ደረስ ምንም አይነት ጨዋታ የለበትም። በመሆኑም ኦውባምያንግ ሰኞ ምሽት በግል የኢንስታግራም ገፁ ላይ የአትሌቶችን የአዕምሮ ብቃት መሻሻልን የሚከታተለውን የአዕምሮ መቆጣጠሪያ መሳሪያ እየተጠቀመ የሚያሳዩ ፎቶዎችን ለጥፏል።


ኦስቲዮፓቲ ምንድን ነው?

በእንቅስቃሴ፣ ሰውነትን በማሳሳብ እና ጡንቻን እና መገጣጠሚያዎችን ማሳጅ በማድረግ የመገጠጠሚያዎችን እንቅስቃሴ ለማሻሻል፣ ጡንቻን ለማፍታታት፣ ደም ወደደምስሮች የሚያደረገውን ዝውውርር ለማፋጠን እና አካልን ከተለያዩ ጉዳቶች ለመፈወስ የሚረዳ አማራጭ የህክምና ዘዴ ነው።

(ምንጭ: ኤንኤችኤስ/NHS)


ማንችስተር ዩናይትድ፣ ዘ ጎልደን ስቴት ኦፍ ዋሪየርስ እና የፈረንሳይ የረግቢ ብሄራዊ ቡድን የዚህን የህክምና ዘዴ መሳሪያዎችን በሰፊው የሚጠቀሙ ደንበኞች ናቸው።

ህክምናው ታካሚዎች ያሉባቸውን በርካታ እንቅስቃሴዎች ላይ በማተኮር እና በጨዋታዎች ላይ የተጫዋቾችን “ንቃትና የውሳኔ አሰጣጥ” በማሻሻል ሚና “ከ20 ዓመታት በላይ በአዕምሯዊሳይንስ” መስኩ ላይ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየም ነው።

ህክምናው ታካሚዎች ቀዝቃዛ እጅጌዎችንና ቁምጠዎችን በመልበስ ከገጠሟቸው ጉዳቶች እንዲያገግሙም ይረዳል። ህመሞችን፣ የጡንቻ መኮማተርና እብጠትን እንዲሁም የደም ዝውውርን በማፋጠን እና ደምን ወደተጎዳው የሰውነት ክፍል በማደርስ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ ዘዴ ያለው ህክምናም ነው።

ኦውባምያንግ አርሰናል ባለፈው ሰምንት ኤሲ ሚላንን ማሸነፍ በቻለበት የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ላይ ያልተሰለፈ ቢሆንም። ነገር ግን አጥቂው ከወዲሁ በዚህ የውድድር ዘመን 30 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ በመጫወት ለአርሰናልና ለዶርትሙንድ በድምሩ 24 ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል።

ጋቦን የፊታችን ሃሙስ ከታይላንድ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ቢኖራትም ዝነኛው ተጫዋቻቸው ኦውባምያንግ ግን ከሁለቱ ልጆቹ ጋር ለንደን እንደሚገኝ የሚያሳይ ፎቶግራፍ በዚያው የኢንስታግራም ገፁ ላይ ለጥፎ ታይቷል።

Advertisements