አዳዲስ የፕሪሚየር ሊግ ክብረወሰኖችን እያስመዘገበ የሚገኘው ሞ ሳላህ

እሱን ከሊዮኔል መሲ ጋር ማነፃፀሩ ከወዲሁ ተጀምሯል። ለምንስ አይነፃፀር? ሳለህ ምንም እንኳ በዚህ የውድድር ዘመን አነስተኛ ጨዋታዎችን ቢያደረግም ከአምስት ጊዜያት የባሎን ዶር አሸናፊው ተጫዋች ሊዮኔል መሲም በላይ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ከዚህም በላይ ሳላህ ከመሲ የሚበልጡ ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ደግሞ በስምንት የጨዋታ ሰዓታት ያነስ በመጫወት፣ በ78 የግብ የማግባት ሙከራ በማነስ እንዲሁም ከደረጃ ሰንጥረዡ በ18 ነጥቦች ዝቅ ብሎ በሚገኝ ቡድን ውስጥ በመጫወትም ጭምር ነው።

እርግጥ ነው የሁለቱ ተጫዋቾች የእግርኳስ ብቃት በአሳማኝ ሁኔታ እንዲነፃፀር ሳለህ አርጄንቲናዊው ተጫዋች ባለፈው ሳምንት ማለፍ የቻለውን 600 ግቦች ማስቆጠር ይጠበቅበታል። ነገር ግን መሐመድ ሳለህ በመሲ ደረጃ እንዲለካ ያደረገው በሊቨርፑል የመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ ይህን ያህል ግቦችን ያስቆጠረ መሆኑ ግን የማይታበይ ሃቅ ነው።

ባለፈው ቅዳሜ በዋትፎርድ ላይ የያስቆጠራቸው ግቦች፣ በተለይም በመሲ ዓይነት ኳስን የማንከባለ አብዶ ያስቆጠረው ግብን ጨምሮ ሳላህ በውድድር ዘመኑ በሊጉ ያስቆጧቸውን ግቦች 28 አድርሶለታል።

ግብፃዊው ምትሃተኛ ለሊቨርፑል በፕሪሚየር ሊጉ በቀሪ ሰባት ጨዋታዎች ላይ አራት ግቦችን ማስቆጠር የሚችል ከሆነም በ38 የውድድር ዘመኑ ጨዋታዎች ላይ ያስቆጠራቸው ግቦች ክብረወሰን ሆነው ይመዘገቡለታል። ሳላህ አራት ተጨማሪ ግቦችን ካስቆጠረ በ2017/18 የውድድር ዘመን የምንጊዜውም የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ግብ ሆኖ ይመዘገብለታል።

ከ20 ግቦች በላይ ለሚያስቆጥር አንድ አጥቂ በሰባት ጨዋታዎች ላይ አራት ግቦችን ማስቆጠር ደግሞ ብዙም የሚቸግር አይመስልም። ሳላህም በውድድር ዘመኑ ይህ ማድረግ ሳይችል ይቀራል ብሎ ማሰብ የሚከብድ ነው።

ተጫዋቹ የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ተሳታፊ ክለቦች ወደ20 ዝቅ ካለበት ጊዜ አንስቶ በአንድ የውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ የማስቆጠሩን ክብረወሰን በጋራ መያዝ የቻሉትን ሶስት ተጫዋቾች (አለን ሺረር በ1995/96 በብላክበርን፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በማንችስተር ዩናይትድ የመጨረሻ የውድድር ዘመኑ 2007/08 እንዲሁም ልዊስ ስዋሬዝ በ2013/14 በሊቨርፑል) መቅደም በሚችልበት እድል እና ጥርጊያ መንገድ ላይ ይገኛል።

ሶስቱ ተጫዋቾች ሳላህ በዚህ የውድድር ዘመን ወደፕሪሚየር ሊጉ ከመምጣቱ በፊት ለረዥም ጊዜያት ማንም ሊደፍራቸው የሚችል የማይመሰሉ 31 ግቦችን አስቆጥረዋል።

ሮናልዶ እና ስዋሬዝ የውድድር ዘመኑ ክብረወሰን የሆነ ግብ ያስቆጠሩበት የውድድር ዘመን ጅማሯቸው ዘገምተኛ ነበር። ሮናልዶ በመጀመሪያዎቹ አራት ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር ያልቻለ ከመሆኑም በላይ ከፓርትስማውዝ ጋር በተደረገ ጨዋታ ላይ በተመለከተው ቀይ ካርድ በቅጣት ምክኒያት ሶስት ጨዋታዎች አምልጠውት ነበር። በአስገራሚ ሁኔታም ሮናልዶ የውድድር ዘመኑን የመጀመሪያ ግቡን ለማስቆጠር እስከመስከረም ወር መጨረሻ ድረስ ስምንት ጨዋታዎችን መጠበቅ ነበረበት።

እንዲሁ ስዋሬዝ የ2013/14 የውድድር ዘመን የመጀመሪያዎቹ አምስት ጨዋታዎች በቅጣት ምክኒያት አምልጠውታል። የውድድር ዘመኑን የመጀመሪያ ግቡን ለማስቆጠርም እስከመስከርም ወር መጨረሻ ድረስ ለመጥበቅ ተገዷል። ስዋሬዝ በየካቲት ወር ላይም በተከታታይ አራት ጨዋታዎች ላይ የግብ ድርቅ ገጥሞት ነበር።

የሳላህ ይህ የውድድር ዘመን በብዙ መልኩ ተመሳሳይነት ያለው ከሺረር 1995/96 የውድድር ዘመን ጋር ነበር። ከመጀመሪያ የክለቡ ጨዋታው አንስቶ ያለማቋረጥ በሁሉም የውድድር ዘመን ጨዋታዎቹ ላይ ግቦችን እያስቆጠረም ይገኛል።

በአንድ የውድድር ዘመን በ38 ጨዋታዎች ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ግብ በማስቆጠር ከ1-10 ባለው ደረጃ (ሳላህ በዚህ ደረጃ ላይ ከወዲሁ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል) ላይ መቀመጥ ከቻሉ ተጫዋቾች በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ዝቅተኛ የግብ ድርቅ የገጠመው ሳላህ ነው። ይህ ማለት እስካሁን ባደረጋቸው ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ብዙም ግብ ያለማስቆጠር ችግር አልነበረበትም ማለት ነው።

ከዚህ ሁሉ በላይ በፕሪሚየር ሊጉ እስካሁን ባለው በየ85.5 ደቂቃዎች ግብ የማስቆጥር አቅም መቀጠል ከቻለ ሳላህ የውድድር ዘመኑ ሲጠናቀቅ ያስቆጠራቸው ግቦች 35 ይደርሳሉ። በመሆኑም በውድድር ዘመኑ ያስቆጠራቸው ከፍተኛ ግቦች በእንግሊዝ እግርኳስ በከፍተኛ ውድድሮች ላይ የሳውዛምፕተኑ ሮን ዴቪስ በ1966/67 የውድድር ዘመን ካስቆተራቸው ግቦች ጋር የሚስተካከል ከፍተኛ ግብ ይሆንለታል። ነገር ግን በ1.3 ሚሊዮን ፓውንድ አንድ ግብ በማስቆጠር ግን ሳላህ የዘመናችን ከፍተኛው ግብ አስቆጣሪ ነው።

ሳላህ ምንም እንኳ የተሰለፈው አነስተኛ ጨዋታዎች ላይ ቢሆንም በሁሉም ውድድሮች ላይ መሲ ካስቆጠራቸው 35 ግቦች በላይ 36 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። እንዲሁም መሲ ካደረጋቸው ሙከራዎች 14.8 በመቶ ያህሉን መረብ ላይ ሲያሳርፍ ሳልህ ግን 22.6 በመቶ ያህሉን የግብ ሙከራዎች መረብ ላይ አሳርፏል።

ሳላህ ያለምንም ጥርጥር ከመሲ ጋር ለመስተከከል ረጅም ርቀት መጓዝ ይጥበቅበታል። ነገር ግን ግብፃዊው ተጫዋች ይህን ብቃቱን በሁለተኛው በሶስተኛው ወይም በአራተኛው እና ከዚያም ባሻገር እንዲዘልቅ ማደረፍ የሚችል ከሆነ በእርግጥም ከዓለማችን ኮከቦች ተርታ እንዲሰለፍ የሚያግደው ነገር አይኖርም።

ሆኖም በዚህ የውድድር ዘመን ከመሲም በላይ ያሳየው ከፍ ያለ ብቃት አስደናቂ ነበር። በ2017/18 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ያስመዘገበው ግብ የማስቆጠር ብቃትም የሊጉ የምንጊዜውም ታላቅ ተጫዋች ሊያሰኘው ይችላል።

Advertisements