የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አስልጣኝ ዲዲየር ዴሾ ለፖግባ በኢንተርናሽናል ብሬክ ምክር እና ድጋፍ እንደሚያደርግለት ገለፀ

Related image

የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሻም ከፖግባ ጋር የፈረንሳይን የአለም ዋንጫ ጉዞ ጥሩ ለማድረግ የክለቡን ችግር እንዲረሳው እንደሚነጋገር ገለፀ።

ፖል ፖግባ ማንችስተር ዬናይትድ ከ ሊቨርፑል ጋር በነበረው የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ላይ በጉዳት ምክንያት ከአሰላለፍ ውጭ ከሆነ በሆላ ለተከታታይ 2 ጨዋታዋች ተቀያሪ ወንበር ላይ ሊቀመጥ ችሏል። እንደ ዲዲየር ዴሾ ገለፃ ከሆነ ፖል ፖግባ ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ጋር ላለበት ቀጣይ ጨዋታዋች ከክለቡ ጋር ያለውን ችግር ቤቱ ውስጥ ትቶ መምጣት አለበት ብሏል።

“ከተለያዬ ተጨዋቾች ያላቸውን ስሜት ለመረዳት ጋር ውይይቶችን አደርጋለሁ ምክንያቱም የሁሉም ሙሉ መረጃ ስለሌለኝ እየጠራሁ አነጋግራቸዋለሁ ” “ከነሱ ጋር ባደረግኩትም ቆይታ ይሄ ኢንተርናሽናል እረፍት ነው በክለባቸው ውስጥ ምንም አይነት ችግር ቢያጋጥማቸው እዚህ ስለሱ ማሰብ አይገባም.”

“ በግልም ይሁን በቡድን ውይይቶችን ማድረግ የአስልጣኝነት ስራዬ ትልቁ ድርሻ ነው ” “ ከፖል ጋር የተፈጠረውን ነገር አላውቅም ፤ ስለእሱ ግን ላነጋግረው ግድ ነው፤ በትክክልም እያንዳንዱን የሚሰራውን ነገር እንዳይመቸው እና ደስተኛ እንዳይሆን ያደረገው ይህ ነው። ”

የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ ከኮሎምቢያ እንዲሁም ከሩሲያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዋችን እንደምታደርግ የሚታወቅ ነው።

Advertisements