የፊዬረንቲና እግር ኳስ ክለብ የልምምድ ቦታቸውን ህይወቱ ባለፈው በቀድሞ አምበላቸው ዴቪድ አስቶሬ ስም ሰይመዋል።

Davide-Astori

ፅሁፍ ዝግጅት መንሀጁል ሀያቲ

የፊዬረንቲና እግር ኳስ ክለብ በ31 አመቱ ህይወቱን ያጣውን የቀድሞ አምበላቸው ለነበረው ለዴቪድ አስቶሬ የልምምድ ቦታቸውን በስሙ መሰየማቸውን አስታውቀዋል።

የፊዬረንቲና ክለብ ሰብሳቢ የሆኑት ማሪዬ ኮኚኚ ለጣሊያን ሚዲያዋች እንደተናገሩት የልምምድ ቦታውን ወደ ” ሴንትሮ ስፖርቲቮ ዴቪድ አስቶሪ ” በሚል እንደተቀየረ ገልፀዋል። ዴቪድ አስቶሪ በጣሊያን ሴሪ ኤ ፊዬረንቲና ከ ዬድኒዜ ሊያደርጉበት በነበረ ጨዋታ ላይ ቡድኑን ለመምራት ስአታት ቀርተውት ሆቴል ውስጥ በተኛበት ሞቶ መገኘቱ የሚታወስ ሲሆን፤ የህክምና ምርመራውም በልብ ችግር ምክንያት ሞቶ እንደተገኘ ተገልፆል።

የቀድሞ ክለቡ የሆነው ካግሊያሪ እንዲሁም ፊዬረንቲና እሱ ሲለብሳቸው የነበሩ ቁጥሮችን ለማንም እንዳይለብሳቸው ማደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የአስቶሪ ቀብር ላይም በሺህዋች የሚቆጠሩ ደጋፊዋች እንዲሁም ከሁሉም የጣሊያን ሴሪ ኤ ቡድኖች የተወጣጡ ተወካዬች በተገኙበት ቀብሩ ተፈፅሟል።

Advertisements