ፖግባ አንድ ቀን ከኔይማር ጎን ቢጫወት ደስተኛ እንደሚሆን ገለፀ

በማንችስተር ዩናይትድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መልካም እንቅስቃሴ ማሳየት የተሳነው ፖል ፖግባ አንድ ቀን ከ ኔይማር ጋር መጫወት እንደሚፈልግ ተናገረ።

ፈረንሳዊው ተጫዋች ወደ ብሄራዊ ቡድኑ የተቀላቀለ ሲሆን የቡድኑ አሰልጣኝ የሆኑት ዲድየር ዴሾ በተጫዋቹ ብቃት ላይ ጥርጥር እንደማያድርባቸው መናገራቸው ይታወሳል።

ፖግባ በማንችስተር ዩናይትድ ከጆሴ ሞሪንሆ ጋር ያላቸው ግኑኝነት ከሻከረ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች የቋሚ ተሰላፊነቱን በየጨዋታው ማግኘት አልቻለም።

የሜዳ ላይ አቋሙም እየወረደ በመምጣቱ ከክለቡ ጋር እያደረገ ያለው ቆይታ ደስተኛ እንዳልሆነ እየተነገረ ይገኛል።

ተጫዋቹ ከአንድ የአርጀንቲና ሚዲያ ጋር ባደረገው ቆይታ አንድ ቀን ከኔይማር ጋር በአንድ ላይ መጫወትን እንደሚፈልግ አሳውቋል።

“አዎ ኔይማርን እወደዋለው።እሱ ሜዳ ውስጥ ደስታ ምን ማለት እንደሆነ ፍቺውን ይሰጣል

“በብራዚል እግርኳስ ህይወታቸው ነው።ሁሉም ሰው ኳስ ይጫወታል።ኔይማር ሲጫወት መመልከት እወዳለው።ያለው ስታይልም የተለየ ነው።ስለዚህ አንድ ቀን አብሬው ብጫወት ደስተኛ ነኝ።”

ፖግባ ልጅ እያለ ዚዳን፣ሜሲ፣ሮናልዶ እና ሮናልዲንሆን ያደንቅ እንደነበር የነ ፔሌ፣ማራዶና እና ካካ ቪድዬም እንዳለው ነገርግን አሁን እንደ ኢኒየስታ፣ደብሩይን፣ያያ ቱሬ እና ሞድሪች አይነት ጠንካራ አማካዮችን እንደሚወድ፣ የተሻለ ተጫዋች ለመሆንም እነሱን እንደሚመለከት አሳውቋል።

Advertisements