ማርሴሎ ሊፒ ሪያን ጊግስ የሰር አሌክስ ፈርጉሰንን መንገድ እንዲከተል ምክር ሰጡ

Image result for ryan giggs wales coach

 

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

ጣሊያናዊዬ የቀድሞ ተጨዋች እና አሁን የቻይናን ብሄራዊ ቡድን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት ማርሴሎ ሊፒ ለዌልሱ አሰልጣኝ ሪያን ጊግስ ምክራቸውን ሰጥተዋል።

የቻይናን ብሄራዊይ ቡድን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት የ69 አመቱ ሊፒ ቻይና ከ ዌልስ ጋር ለምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ፤ በዌልስ አሰልጣኝነት ዘመኑ የመጀመሪያውን ጨዋታ ለሚያደርገው ለማንችስተር ዬናይትዱ ሌጀንድ እንዲሁም የአሁኑ የአሰልጣኝ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል.

” ለእሱ ምክር መስጠት ይገባኛል ብዬ ባላስብም, ከዚህ በፊት በማንችስተር ዬናይትድ ውስጥ ከምንጊዜም ምርጡ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር መስራት ችሏል ፤ ስለዚህ ማድረግ የሚገባው በዛስአት ላይ የተማረውን ነገር ነው መስራት ያለበት።

” ማርሴሎ ሊፒ ማርሴሎ ሊፒ የአለም ዋንጫውን እና የቻምፒዬንስ ሊጉን ዋንጫ ማንሳት ከቻሉት ብቸኛ ሁለት አሰልጣኞች መካከል አንዱ ናቸው፤ የአለም ዋንጫን ከጣሊያን ቡድን ጋር እና የቻምፒዬንስ ሊጉን ዋንጫ ከጁቬንቱስ ጋር ማንሳት ችለዋል. በተመሳሳይ መልኩ ጊግስ ማርሴሎ ሊፒን የምንጊዜም ምርጡ አስልጣኝ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታዬን ስለማደርግ ደስ ብሎኛል ተናግሯል።

Advertisements