በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅ/ጊዮርጊስ ከካራ ብራዛቪል ጋር ተደለደለ 

በካፍ ቻምፕየንስ ሊግ በዩጋንዳው ሻምፕዮን ኬሲሲኤ ተሸንፎ ወደ ምድብ ድልድሉ መግባት ያልቻሉት ፈረሰኞቹ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከኮንጎው ካራ ብራዛቪል ጋር ተደለደለ።

ፈረሰኞቹ ለተከታታይ ሁለተኛ አመት በቻምፕየንስ ሊጉ የምድብ ድልድል ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉበት ወርቃማ አጋጣሚ በኬሲሲኤ ተነጥቀዋል።

የዩጋንዳው ተወካይ በመጀመሪያው ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ያለ ጎል ከተለያየ በኋላ በሜደው 1-0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ምድብ ድልድሉ ተቀላቅለዋል።

ቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎቹን ይክስበታል ተብሎ የሚታሰብበት ሌላ መድረክ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ በመሳተፍ ይቀጥላል።

ወደ ምድብ ድልድሉ ለመግባትም ምሽት ላይ በግብፅ ካይሮ በወጣው ድልድል የመጨረሻ ተጋጣሚውን ያወቀ ሲሆን ቡድኑም የኮንጎው ካራ ብራዛቪል መሆኑ ታውቋል።

የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ በምድብ ድልድል ውስጥ የሚካተት ሲሆን የመጀመሪያ ጨዋታቸውንም በቀጣዩ ወር እንደሚደረግ ይጠበቃል።

Advertisements