ኡስማን ዴምቤሌ በባርሴሎና ቤት የመጨረሻውን ፈተና ማለፍ አለበት – ዣቪ

Image result for demble

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

የቀድሞው የባርሴሎና ተጨዋች ዣቪ ኸርናንዴዝ በከፍተኛ ገንዘብ ባርሴሎናን የተቀላቀለው ዴምበሌ ጫናውን መቋቋም እንደሚችል በደንብ እራሱን ማሳየት አለበት ሲል ተናገረ ።

ኡስማን ዴምበሌ በባርሴሎና እራሱን ማረጋገጥ እና 105 ሚሊዬን ፖውንዱ እንደሚመጥነው ለማሳየት የመጨረሻ ፈተናውን ማለፍ ግድ ይለዋል ይላል ዣቪ። ዣቪ ለ ሶ ፉት በሰጠው አስተያየት ፦ ” እሱ ጊዜ ያስፈልገዋል፤ ለማንኛውም ተጨዋች ባርሳ የመጨረሻ ፈተና ነው፤ ይህንን ማለፍ ከቻለ ለእሱ ልክ እንደ ማስተር ዲግሪ ነው ምክንያቱም ማንኛውም ተጨዋች የሚጫወትበት ክለብ አይደለም።”

“ዴምቤሌ ልዬ የሆነ ችሎታ አለው, በጣም ፈጣን ነው ነገር በዶርትሙንድ እና በሬንስ የነበረውን ቦታ ማግኘት አልቻለም, እዛ ብዙ ቦታ አግኝቷል ብዙ ጊዜም ነበረው።” ” ፈጥኖ መማር አለበት, በአእምሮው ጠንካራ መሆን አለበት ለራሱ እኔ የባርሳ ተጨዋች ነኝ ብሎ ማሰብ አለበት፤ የሰነ ልቦና ጥንካሬ ያስፈልገዋል።”

ፈረንሳያዊዬ ኢንተርናሺናል ከቦርሺያ ዶርትሙንድ 2017 በክረምቱ የዝውውር መስኮት ባርሳን የተቀላቀለ ሲሆን ከጉዳት ጋር በተያያዘ ለወራት ከሜዳ እርቆ ነበር።

Advertisements