ፍጥጫ / በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ድልድል ታሪክ ሰሪው ወላይታ ዲቻ ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ ተገናኘ

የአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጥሎ ማለፍ ፍልሚያ ድልድል ይፋ ሲደረግ ታሪክ ሰሪው ወላይታ ዲቻ ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ ተገናኝቷል።

ከዲቻ በተጨማሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያካተተው ድልድሉ ከቻምፒዮንስ ሊጉ ተሰናብተው በኮንፌድሬሽን ዋንጫው የተገኙትን ፈረሰኞቹን ከዲሞክራቲክ ኮንጎው ካራ ብራዛቪል ጋር አገናኝቷል።

በምሽቱ እጣ አወጣጥ ስነስርዓት ከሰሞኑ የግብፁን ሀያል ዛማሊክን በመርታት ወደቀጣዩ ዙር ያለፈው ወላይታ ዲቻ ከታንዛኒያው ጠንካራ ክለብ ያንግ አፍሪካ ጋር ተደልድሏል።

ምስረታውን በ 1935 ያደረገው የታንዛኒያው ክለብ 27 የሀገሩን የፕሪምየር ሊግ ዋንጫዎች በመውሰድ ቀዳሚ ቢሆንም በአፍሪካ የክለብ ውድድሮች ላይ ያማረ ታሪክ የለውም።