“በዩናይትድ አቋሜ ዙሪያ መሻሻልን ማየት እፈልጋለሁ” – አሌክሲስ ሳንቼዝ


አሌክሲስ ሳንቼዝ ወደማንችስተር ዩናይትድ ካደረገው ዝውውር በኋላ እያሳየ ባለው አቋም ዙሪያ የተሻለ ነገር መመልከት እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡ 

ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ኢምሬትስን በመልቀቅ ወደ ኦልትራፎርድ የመጣው ቺሊያዊው አጥቂ 10 ጨዋታዎችን አድርጎ ማስቆጠር የቻለው አንድ ጎል ብቻ ነው፡፡ 

የ 29 አመቱ ተጫዋች የብሔራዊ ቡድን ግዴታውን ለመወጣት ስዊድን ባለበት ከሀገሩ አንድ ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታም ከአርሰናል የአራት ዓመታት ህይወት በኋላ በዩናይትድ ያለውን አዲሱን ጊዜ ለመልመድ እየታገለ መሆኑን የመነበትን አስተያት ሰጥቷል፡፡    

ሳንቼዝ ሲናገር “እኔ እራሴን የምፈልግ አይነት ሰው እንደመሆኔ ከዚህ የተሻለ ነገር እንዲኖረኝ እጠብቃለሁ፡፡ ወደዩናይትድ ከመጣሁ በኋላ ሁሉንም ነገር በፍጥነት መቀየር ከባድ ነው፡፡ ወደዚህ ወደስዊድን መምጣት እራሱ አልፈለኩም ነበር፡፡

“ክለብ መቀየር ቅፅበታዊ ነገር ነው፡፡ በጥር የዝውውር መስኮት ክለብ ስቀይር የመጀመሪያ ጊዜዬ ነው፡፡ ነገርግን በህይወቴ አስቸጋሪ የሆኑ ብዙ ለውጦች አጋጥመውኛል፡፡” ሲል በዩናይትድ እራሱን ለማሳየት ጊዜ እንደሚስፈልገው ለማስረዳት ሞክሯል፡፡

ቺሊ ከሩሲያው ዓለም ዋንጫ ውጪ መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን ሳንቼዝም ከሀገሩ ብሔራዊ ቡድኑ አምበል ክላውዲዮ ብራቮ ጋር ተነጋግሮ ሀሳቡን ባይቀይር ኖሮ በመጪው ቅዳሜ በስዊድን ስቶኮልም ከሚደረገው የወዳጅነት ጨዋታ እራሱን ያገል እንደነበር አይይዞ ገልል፡፡

ሳንቼዝ  “ከጨዋታው ውጪ እንድሆን ፍቃድ እንዲሰጠኝ ጠይቄ ነበር፡፡ ነገርግን በጉዳዩ ላይ ከክላውዲዮ ጋር ብነጋገር የተሻለ እንደሆነ አሰብኩኝ እና እሱን አወራሁት እሱም ሁላችንም በአንድነት መቆም እንዳለብን ነገረኝ፡፡” ሲል ከወዳጅነት ጨዋታው ራሱን ሊያገል ጫፍ የደረሰበትን አጋጣሚ አስታውሶ ተናግሯል፡፡

የዩናይትዱ የፊት መስመር ተጫዋች ለቺሊ 119 ጨዋታዎችን አድርጎ 39 ግቦችን ማስቆጠር ሲችል በ 2015 እና 2016 ከሀገሩ ጋር ተከታታይ ሁለት የኮፕ አሜሪካ ዋንጫዎችን ማንሳቱ አይረሳም።

Advertisements