ዌልሳዊው ጋሪዝ ቤል የሀገሩን የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ሪከርድ ሰበረ

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

ጋሬዝ ቤል ሪከርድ ሲሰብር ሪያን ጊግስ በዌልስ አሰልጣኝነቱ የመጀመሪያ ድሉን አጣጥሟል።

የማድሪዱ የፊት መስመር ተጨዋች የሆነው ጋሬዝ ቤል ሀገሩ ዌልስ ከቻይና ባደረገችው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ሀትሪክ በመስራት በኢያን ራሽ ተይዞ የነበረውን የከፍተኛ ጎላ አስቆጣሪነት ሪከርድ መስበር ችሏል።

ከዚህ በፊት የዌልስ የምንግዜም የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን በ28 ጎል በማስቆጠር በኢያን ራሽ ተይዞ የነበረ ሲሆን አሁን 29 ጎሎችን በማስቆጠር ጋሬዝ ቤል መረከብ ችሏል።

ግሬዝ ቤል ሪከርድ በሰበረበት ጨዋታ ላይ በዌልስ አሰልጣኝነት የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው የቀድሞው የማንችስተር ዬናይትድ ሌጀንድ ሪያን ጊግስ ቻይናን 6 ለ 0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።

Advertisements