ዌስትሃም ዬናይትድ ከበርንሌ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ሜዳ ውስጥ በመግባት ሜዳውን የወረሩትን ደጋፊዋች ላይ የህይወት ዘመን እገዳ አስተላለፈ

Image result for west ham fans at burnley game

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

መዶሻዋቹ በሜዳቸው በርንሌን አስተናግደው ሶስት ለዜሮ በሆነ ውጤት በተሸነፉበት ጨዋታ ላይ ወደ ሜዳ ዘለው በመግባት ረብሻን በፈጠሩ ደጋፊዋች ላይ ዳግም ወደ ሜዳ እንዳይገቡ እገዳ አስተላልፏል።

በጫዋታው ላይ ሳንቲሞችን እንዲሁም የተለያዬ ቁሳቆሶችን በመወርወር ለመጉዳት ሙከራ ያደረጉ ዳጋፊዋች ላይ የእድሜ ልክ እገዳ ያደረጉ ሲሆን፤ የክለቡ ባለድርሻ የሆኑትን ዴቪድ ሱሊቫንም በሳንቲም የተመቱበት አጋጣሚ ነበር። ክለቡም ፈጣን እና ቁርጥ ያለ ውሳኔ እንደወሰደ ያሳወቀ ሲሆን የክለቡ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ኬረን ባርዲ ስለተፈጠረው ነገር ይቅርታ በመጠየቅ ” በክለቡ ታሪክ የምንግዜውም አሳዛኝ ቀን ብለውታል።”

ይህንንም ውሳኔ የወሰኑት ባለፈው ሳምንት በተደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ሲሆን በስብሰባ ላይ የክለቡ ተወካዬች፤ ፖሊስ ፤ የስቴዴየሙ ባለቤቶች በአጠቃላይ የለደን ስታዲዬም የጥበቃ አማካሪ ቡድን በመሆን ነው ውሳኔውን ያስተላለፉት። ከዚህ በሆላ የሚፈጠር እንደዚህ አይነት ችግር ሙሉ ለሙሉ እስቴዲየሙ ለመዘጋት እንደሚያደርግ ማስጠንቀቂያም ሰጥተዋል።

Advertisements