“ውስን ተጫዋቾች ብቻ ስኬታማ የሚሆኑበት” የሪያል ማድሪድ የታዳጊዎች ማሰልጠኛ

ሪያል ማድሪዶች የዓለማችን የዝውውር ሪከርድን መስበር ከምንም በላይ ደስተኛ ቢያደርገቸውም፣ ነገር ግን “በአንድ የእግርኳስ ክለብ ሁሉንም ግብዓቶች በማሟላት የተገነባ የምንጊዜውም ታላቅ” ማሰልጠኛ ለመገንባት ሲሉ 100 ሚሊዮን ዩሮ መዋዕለ ንዋይ ወጪ አድርገዋል።

ተከታዩ ፅሁፍም የዓለማችን ስኬታማው እና ታላቁ የስፔን ክለብ ሪያል ማድሪድ ውስን ታዳጊ ተጫዋቾች ብቻ ስኬታማ የሚሆኑበትን የታዳጊዎች ማሰልጠኛን በሰፊው ተመልክቷል።

ማርኮ አሴንሲዮ ከ25 ያርድ ርቀት ላይ የመታው እንደሮኬት በሚወነጨፍ ኳስ ከማኑኤል ኑየር ፊት እየተምዘገዘገ የታችኛው የመረቡ ስር ከማረፉ በፊት የጨዋታውን ውጤት የሚያሳየው ሰሌዳ 2ለ2 የሚል ውጤት ያሳይ ነበር። ጀርመናዊው ግብ ጥባቂም ኳሷን ለመቆጣጠር ሳይችል ቀረ። የካዴቴ ቢ ተጫዋቹ በሊግ ውድድሮች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተገመገመ መጫወቱ ጨዋታው ከመጀመሩ አራት ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንኳ በዚህ ጨዋታ ላይ እጫወታለሁ የሚል የመዝናናት ስሜት እንዲሰማው አላደረገውም። በፊፋ ውድድር ላይ መጫወቱም ይህን ግብ ያስቆጠረበትን ዘዴ በሚገባ እንዲተገብርም አላደረገውም።

ተፎካካሪነት በሪያል ማድሪድ የስልጠና ማዕከል የስራ ባልደረቦች ዘንድ የሚበረታታ ነገር እንደሆነ የሚናገሩት የማስለጠኛ ማዕከሉ አሰልጣኝ የሆኑት ኻቪየር ሞራን “ሪያል ማድሪድን የሚወክሉ ተጫዋቾች አሉ። ከልባቸው ሪያል ማድሪድን የሚወክሉ። በዚህ ስኬታማ ለመሆንም የግድ በራሳቸው ላይ እርግጠኛ መሆን ይጥበቅባቸዋል። ከፍተኛ ፍላጎትን የምታለማምደው ነገር አይደም። ነገር ግን ልጆቹን በተነሳሽነትና በእምነት እንዲታጠሩ ልታደርጋቸው ትችላለህ። የክለባችን መፈክር “ፈፅሞ እጅ አትስጥ” የሚል ነው። ስለዚህ ያን ዒላማቸውን ለመምታት ያ ዓይነቱ ጫፍ የደረሰ ተፎካካሪነት የግድ ያስፈልጋቸዋል።” ሲሉ ገልፅዋል።

ተጫዋቾች እንደማንኛውም ተጫዋች ከልምምድ በኋላ በክፍላቸው ውስጥ አረፍት ሲወስዱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ሲተላለፍ በክፍሎቹ መተላለፊያ ግድግዳዎች ላይ የአልፍሬዶ ዲ ስቴፋኖ፣ ዚነዲን ዚዳን እና ራኡል ምስሎች ይተዩ ነበር። ነገር ግን ከእነዚህ ተጫዋቾች መከከል በሪያል ማድሪዱ ላ ፋብሪካ (ፋብሪካው) በተሰኘው የወጣቶች ማሰልጠኛ የተጫወተው ተጫዋች አንዱ ብቻ ነው። ክለቡም በቅርብ ጊዜያትም ከአበይት የዝውውር ፊርማዎች ጨርሶ አልራቀም። ሪያል ማድሪድ ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ በ2000 ክለቡን በፕሬዝዳንትነት ከተረከቡበት እና ጋላክቲኮውን ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ለአምስት ጊዜያት ያህል የዓለማችንን ከፍተኛ የዝውውር ክብረወሰን ሰብሯል። እናም ታዲጊዎቹ ከዚህ ዝውውር በላይም ልቀው መገኘት እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ስፔን በ2010 የዓለም ዋንጫን ስታነሳ የሪያል ማድሪድ የእግርኳስ ማሰልጠኛ ያፈራቸው የነበሩት ኹዋን ማታ፣ አልቫሮ አርቤሎዋ እና ኢከር ካሲያስ ብቻ ነበሩ። በአንፃሩ ግን ከ23ቱ የዚህ ቡድን ስብስብ ተጫዋቾች ዘጠኙ የተገኙት ከዝነኛው የባርሴሎና እግርኳስ ማሰልጠኛ ከሆነው ላ ማሲያ ነበር።

“ሪያል ማድሪድ ለብሄራዊ ቡድን መጫወት የሚችሉ ተጫዋቾችን በማፍራት የሚታወቅ ክለብ የመሆን ፍላጎት አለው። ” ሲሉ ሞራን ተናግረው። “ተጫዋቾችን ስንመልመል በቴክኒክ ረገድ ፍፁም ተሰጥኦ ያላቸውን እና የተለያዩ የታክቲካዊ እና የስትራቴጂካዊ ዘዴዎችን መላመድ የሚችሉ ልጆች እንደሚያስፈልጉን እናውቃለን። ከባርሳ እና ከሌሎች እንለይ የነበረውም በማንኛውም ዘዴ ላይ መጫወት የሚችሉ ምሉዕ ተጫዋቾችን ለመፍጠር በምናደርገው ዘዴ ነበር።

“በየጊዜው አሰልጣኞች በሚመጡነት እና በሚሄዱበት የመጀመሪያው ቡድን በዋናነት ልትቀይረው ስለምትችለው ነገር ፈፅሞ የምታውቀው ነገር የለም። ስለዚህ ለእያንዳንዱ ተጫዋች አንዳች ግላዊ ማንነት ከመፍጠር ይልቅ ይበልጥ በግለሰቦች ላይ ትኩረት ለማድረግ እንሞክራለን። መላመድ ጉልህ የሆነ የህይወታችን አካል ነው። እናም እነዚያ ልጆች በእግራቸው ማሰብ ስለመቻላቸው እና በሽርፍራፊ ሰከንዶች ላይ ለሚለዋወጡ ነገሮች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችሉ ስለመሆናቸው እርግጠኞች መሆን ይኖርብናል። ይህ ደግሞ በእግርኳስ ላይ ሁልጊዜም የሚሆን ነገር ነው።” ሲሉ ለሃሳባቸውን ማጠናከሪያ ነው ያሉትን ሃሳብ አብራርተዋል።

ሪያል ማድሪድ ከተማ የተሰኘውና “በአንድ የእግርኳስ ክለብ የተገነባ የምንጊዜውም ታላቅ የስፖርቶች አቅርቦት ያለው ማዕከል ስራ የጀመረው በ2005 ነበር። በርካታ አገልግሎቶች ያሉት ማዕከሉ ከሳንቲያጎ በርናባው ስታዲየም 40 እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን፣ በአንድ ቀን ሁሉንም የላ ሊጋ ክለቦች ማስተናገድ የሚችል በቂ የሆነ የመልበሻ ክፍሎች ጨምሮ፣ በርካታ ጂሞች፣ ክፍሎች፣ የስብሰባ አዳራሾች እና ቢሮዎች እንዲሁም የውሃህክምና የሚሰጥ የውሃ ገንዳ፣ የህክምና ማዕከል እና ጋዜጣዊ መግለጫ መስጫ ክፍል አሉት። የመጫወቻ ሜዳው በሳንቲያጎ በርናባው አገልግሎት እየሰጠ ከሚገኘውና ከኔዘርላንድ ከመጣው ሳር ጋር ተመሳሳይ ነው።

ክለቡ ከርቀት ለሚመጡ ወጣት ሰልጣኞቹ የትምህርት አቅርቦት እና መጓጓዣ ከማመቻቸቱም በላይ ለ40 ተጫዋቾች የመኖሪያ ቤት አለው። ተጫዋቾቹ በማዕከሉ በአማካኝ ለሶስት ዓመታት የሚቆዩ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የ10 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ታዳጊ ልጆች ወደክለቡ ማሰልጠኛ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደደረሱ “ከዚህ ወዲህ የወላጆቻችሁ ልጆች አይደላችሁም። እናንተ አሁን የሪያል ማድሪድ ተጫዋቾች ናችሁ።” ይባላሉ። ይህ ደግሞ በኃያሉ ክለብ ፈፅሞ የማይዘነጉት አንዳች ዋጋ ያለው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ስንቅ ይሆናቸዋል።

አትሌቶች በትክክለኛው ጊዜ የብቃታቸው ጫፍ ላይ እንዲደርሱ ሲባል ትክክልኛ የልምምድ ስትራቴጂ የሚነደፍበት ሂደት የሆነው ፔሪዮዲሴሽን የተባለው የልምምድ ሂደት በስፔን እግርኳስ ላይ በጣም ከፍ ያለ ፋይዳ አለው። እንደምሳ ሰዓት ያሉ ቀላል ጉዳዮች እንኳ ከ40 ደቂቃ በላይ አይቆዩም። ሌሎች የዕለቱ የምግብ ሰዓቶችም በከፍተኛ ትኩረት ውስን ጊዜ የሚሰጣቸው ናቸው። የማለዳ ስፖርቶችም ከዕለቱ የልምምድ በፊት በታዳጊዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ተለምዷዊ ተግባራት ናቸው። ጨዋታ በማይኖሩባቸው ቀናትም “የማከካሻ ስራዎች” በዕለቱ የልምምድ የትግበራ ዕቅድ ውስጥ የሚገቡ ናቸው። በቀሪዎቹ የዕለቱ የልምምድ ጊዜያትም ተጫዋቾች ሳምንቱን ሙሉ የአካል እና የታክቲክ ማዳበሪያ ልምምዶች በሂደት ይሰጧቸዋል። የኳስ አጨራረስ፣ አዟዟር እና ድንገተኛና ፈጣን እንቅስቃሴዎች በመጨረሻው ልምምድ ላይ ከጨዋታ በፊት ቅድሚያ ትኩረት የሚያገኙ ተግባራት ናቸው።

በታክቲክ ረገድም አሰልጣኞች የጨዋታ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በመላምት ላይ ተመስርተው ልምምድ ይሰጣሉ። ሁልጊዜም ልምምድ በፉክክር መንፈስ የመከላከል እንቅስቃሴን ሰብሮ የመግባት ዘዴ እንዲያዳብሩም ማብራሪያ ይሰጠቸዋል። የተጫዋቾች የጨዋታ ላይ የቦታ አያያዝ ወሳኝ ጉዳይ ሲሆን፣ በዚህ ላይም አሰልጣኞች ፍፅምና እንዲኖር ይተጋሉ። ተጫዋቾች ጨዋታው አምስት ደቂቃ እስኪቀረው ድረስ 1ለ0 እየመሩ እንዳሉ በማሰብ ከፍተኛ ጫናን እንዴት መቋቋም እንዳለባቸው ጭምር ይነገራቸዋል። አጥቂዎችም በእያንዳንዱ የኳስ ቅብብላቸው ላይ ትዕግስት እንዲኖራቸው እና የተከላካይ ክፍልን እንዴት በፍጥነት ሰብረው መግባት እንዳለባቸውም ይብራራላቸዋል። ተጫዋቾች ሁለት ለአንድ በሆነ እንቅስቃሴ ላይ ተቃራኒ ተጫዋቾችን እንዴት ከእንቅስቃሴ ውጪ ማድረግ እንደሚኖርባቸውም መመሪያ ይሰጣቸዋል። እንደብሄራዊ የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች ሁሉ የታክቲክ ሰሌዳዎችን መጠቀምም በማሰልጠኛው ላይ የተለመደ ዘዴ ነው።

ለስህተት የጥፋተኝነት ስሜት መሰማት በዚህ የልምምድ ሜዳ ላይ ዋጋ ቢስ ነው። በዚህ የልምምድ ሜዳ ሰብሮ ለመውጣት እና በሳንቲያጎ በርናባው መጫወት የመቻል ዕድል ለማግኘት ፍፁም የሆነ ብቃት ማሳየት የግድ ይላል። በሚገርም ሁኔታም ይህን ማሳካት የሚችሉት እና የሪያል ማድሪድን ዋና ቡድን መቀላቀል የሚችሉ በጣት የሚቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

Advertisements