” ጭንቅላት ያለው ሰው ስለ ስፖርት ለሚያውቅ ሰው ቡድኑ በሽግግር ላይ ነው ያለው ብሎ ሊያስብ ይገባል”- ጆዜ ሞሪንሆ

Image result for jose mourinho

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

በአጨዋወት ፍልስፍናቸው ከቡድናቸው ደጋፊዋች እንዲሁም ኳስን ከሚውዱ ሁሉ ትችትን እያስተናገዱ የሚገኙት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ማንችስተር ዬናይትድ በሽግግር ወቅት ላይ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በላሊጋው ክለብ ሲቪያ በደርሶ መልስ ሁለት ለአንድ በሜዳቸው ተሸንፈው ከሻምፒዬንስ ሊጉ ውጭ የሆኑት ጆዜ ከሲኤንኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ሰፋ ያለ አሰተያየቶችን ሰጥተዋል፤ ፦ ” ከአውሮፖ ሻምፒዬንስ ሊግ ውጭ ተሸንፎ መውጣት ያለውን መከፋት ይገባኛል ከዛ ውጭ ያለው ነገር ግን ምንም አይገባኝም።”

” በእንግሊዝ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ በእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በጣም ትልቅ ክለብ ቢኖር በተደጋጋሚ የተለያዬ ዋንጫዋችን ያነሳ በአሁን ስአት ላይ በሽግግር ጊዜ የሚሆንበት ስአት አለ ይህ የክለብ አንዱ አካል ነው።”

” ተመልከቱ በፕሪሚየር ሊጉ ከፊት ለፊታችን ያለው አንድ የተሻለ ክለብ ነው 18ቱ ከእኛ በሆላ ነው ያሉት ፤ ወደ ፊት 19 ክለቦች ከሆላችን እንዲሆኑ እንፈልጋለን ይህ እውነታው ነው፤ ጭንቅላታ ላለው ሰው, ስለ ስፖርቱ እውቀት ላለው እና ለሚያውቀው እውነታው ማንችስተር ዬናይትድ በሽግግር ጊዜ ውስጥ ነው ያለው።”

ጆዜ ሞሪንሆ በማንችስተር ዬናይትድ በመጀመሪያው የአሰልጣኝነት ዘመናቸው የአውሮፖ ሊግ እንዲሁም የሊግ ካፕ ዋንጫን ማንሳታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ስለ ክለቡ የተናገሩት ንግግር ብዙዋችን እንዳስከፋ የሚታወስ ነው።

Advertisements