“ሜሲ ምንም አይነት ነገር ማረጋገጥ አይጠበቅበትም ” – ማራዶና

Image result for messi maradona

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

አርጀንቲናዊዬ የኳስ ጠቢብ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና የሀገሩ ልጅ የሆነውን ሊዬኔል ሜሲ ስለምንም ነገር ሳይጨነቅ በጨዋታው መዝናናት ነው ያለበት በማለት ሀሳቡን ሰጥቷል።

የ1986ቱን የአለም ዋንጫ ማንሳት የቻለው ማራዶና የ5ጊዜ የባላንዶር አሸናፊ የሆነው አርጀንቲናዊዬ የኳስ ምትሀተኛ ሌዬኔል ሜሲ እስካሁን የተቸገረበትን የአለም ዋንጫውን አንስቶ የምንጊዜም ምርጥ መሆኑን ማሳየት አለበት የሚለው ትችት ሊሳስበው እንደማይገባ ገልፃል። መሲ በክለቡ ባርሴሎና ያላሳካው የክብር አይነት የለም ላሊጋውን፤ የሻምፒዬንስ ሊግ ዋንጫ እንዲሁም ሌሎችን ማንሳት ችሏል። ማራዶና በሰጠው ሀሳብም ፦ ” እኔ እሱን ልመክረው የምችለው ነገር ዝም ብሎ ጨዋታውን እንዲጫወት እና በጨዋታው እንዲዝናና ነው።”

” የአለም ዋንጫውንም ሆነ ሻምፒያንስ ሊጉን አሸነፈም አላሸነፈም ትችቶችን ወደ ጎን በመተው ጨዋታው ላይ ማተኮር ይገባዋል።” “ምንም ነገር ማረጋገጥ አይጠበቅበትም ፤ሜዳ ላፕ በጨዋታው መዝናናት ብቻ።”

እንደሚታወቀው ሊዬኔል ሜሲ የ2014ቱ የአለም ዋንጫ ሀገሩን ለፍፃሜ ማድረስ ቢችልም በጀርመን ተሸንፎ ዋንጫውን ሳያገኝ ወደ ሀገሩ መመለሱ የሚታወስ ነው፤ መሲ በሩሲያው የአለም ዋንጫ ተሳክቶለት ምንጊዜም የሚናፍቀውን ዋንጫ ወደ በሀገሩ ስም ያስመዘግብ ይሆን?

Advertisements