ተተኪ / የቀድሞው የዶርትሙንድ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሼል ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ለመሆን ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ

የቀድሞው የቦሩሲያ ዶርትሙንድ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሼል የአርሰናል አሰልጣኝ ለመሆን መስማማታቸው ተገለፀ።

ቱሼል ባሳለፍነው አመት ግንቦት ወር ላይ ከዶርትሙንድ ከተሰናበቱ በኋላ ስራ አጥ ሆነው የቆዩ ሲሆን ባየር ሙኒክም የ 44 አመቱን አሰልጣኝ የጁፕ ሄንክስ ተተኪ አድርጎ ለማምጣት ፍላጎት እንዳለው ሲነገር ቆይቷል።

ነገርግን የእንግሊዙ ሜትሮ ከጀርመን የወጡ ዘገባዎችን እማኝ አድርጎ እንደፃፈው ቱሼል ለሙኒክ ከጀርመን ውጪ ያለ ክለብ ማሰልጠን እንደሚፈልጉ መናገራቸውንና ወደፕሪምየር ሊግ ለማምራት መቃረባቸው ይፋ ሆኗል። 

ዘገባው እንደሚለው ከሆነ ቱሼል በዌስትፋለን ከሴቨን ሚስሊንታት ጋር መልካም የሚባል ግንኙነት ያልነበራቸው ቢሆንም የቀድሞ የስራ ባልደረባቸውን እግር ተከትለው ወደሰሜን ለንደን ለመምጣት ጫፍ ደርሰዋል።

ባሳለፍነው አመት አርሰናልን በተጫዋቾች ምልመላ ሀላፊነት የተቀላቀሉት ሚስሊንታት በዶርትሙንድ ቆይታቸው ወደክለቡ የልምምድ ስፍራ እንዳይገቡ እገዳ ተጥሎባቸው እንደነበር አይረሳም። 

Advertisements