ግዳጅ / መሱት ኦዚል የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተልዕኮውን በማቋረጥ ወደክለቡ አርሰናል ተመለሰ

ፅሁፍ ዝግጅት : መንሀጁል ሀያቲ

መሱት ኦዚል የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ግዳጁን ሳያጠናቅቅ ወደእንግሊዝ ተመልሶ ክለቡ አርሰናልን ተቀላቅሏል።

በአገራት የወዳጅነት ጨዋታ ሀገሩ ጀርመን ከስፔን ጋር ባደረገችውና  1-1 በተጠናቀቀው ጨዋታ ላይ ሙሉ 90 ደቂቃ ተሰልፎ መጫወት የቻለው መሱት ኦዚል የብሄራዊ ቡድን ቆይታውን አቋርጦ ወደ አርሰናል ተመልሷል።

የመድፈኞቹ ጨዋታ አቀጣጣይ በቀጣይ ከብራዚል ጋር የሚደረገው የወዳጅነት ጨዋታም የሚያልፈው ሲሆን ከቡድኑ ውጭ የሆነበት ምክንያትም በጉዳት ሳይሆን የጀርመን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዩአኪም ሎው እረፍት ሊሰጡት ፈልገው እንደሆነ ተገልጿል።

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከብራዚል ብሄራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርግ ሲሆን ሎው በሰጡት አስተያየትም ከስፔን ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ የተጠቀሟቸውን ተጨዋቾች መሉ ለሙሉ እንደማይጠቀሙና በአዲስ ቅያሪ እንደሚገቡ አስታውቀዋል።

Advertisements