​ለምን / በማንችስተር ዩናይትድ ቤት እንዴት የፖል ፖግባ እና ጆዜ ሞሪንሆ ግንኙነት ሊሻክር ቻለ?


ፅሁፍ ዝግጅት : መንሀጁል ሀያቲ

ጆዜ ሞሪንሆ በኦልድትራፎርድ ለወራት በፖል ፖግባ ደስተኛ አልሆኑም። 

የአሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ እና የፖል ፖግባ ግንኙነት መሻከር የጀመረው የያዝነው የውድድር ዘመን እንደተጀምረ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ፖግባ የአሰልጣኙን ትእዛዝ ባለመቀበሉ እንደሆነ ዘገባዋች ይገልፃሉ።

ፖል ፖግባ ባለፉት ጊዜያት ዬናይትድ ካደረጋቸው 11 ጨዋታዋች ውስጥ መሰለፍ የቻለው በ4ቱ ጨዋታዋች ላይ ሲሆን ጉዳት እንዲሁም ያለበት ደካማ አቋም ከሰባቱ ጨዋታዋች ውጭ አድርገውታል።

እንደ ዘ ሰን ዘገባ ከሆነ ጆዜ ፖል ፖግባ በጥቅምት ወር ላይ ባጋጠመው ጉዳት የተደረገው የህክምና ክትትል እንዳላስደሰታቸው እና በዚህም ደስተኛ እንዳልሆኑ ይገልፃል።

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ፖግባ ጉዳቱ ባጋጠመው ስአት ህክምናውን ማንችስተር ውስጥ ቁጭ ብሎ እንዲከታተል ቢነግሩትም ፖል የጆዜን ምክር ወደ ጎን በመተው ጉዞውን ወደ ሚያሚ አደርጓል፤ ይህም ጆዜ ሞሪንሆ በጣም ያስከፋ ጉዳይ ነበር።

በማንችስተር ውስጥ የሚገኙ የ ዘ ሰን ምንጮችም ከላይ የተጠቀሰው ምክንያት ለአስልጣኙ እና ለፖል ፖግባ አለመስማማት ትክክለኛ ምክንያት እንደሆነ ገልፅዋል።

የእውነትም ነገሩ እየከረረ ከሄደ እና የዬናይትድ ደጋፊዋች ኮከባቸውን ሜዳ ላይ ለተከታታይ አለመመልከታቸው ሲያስከፋቸው፤ የኦልድ ትራፎርድ ሀላፊዋች ምርጫቸው ምን ይሆን? 

ጆዜን ማባረር ወይስ ፖግባን መሸጥ? ወደፊት የምንመለከተው ይሆናል።

Advertisements