የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በፕሪሚየር ሊጉ የቪዲዬ ዳኝነት ሲስተምን መጠቀም ሊጀምር ነው

Image result for video assistant referee

 

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የቪዲዬ ዳኝነት ሲስተምን መጠቀም ሊጀምር መሆኑን ሊያሳውቅ ነው ነገር ግን አንዳንድ ክለቦች የቪዲዬ ዳኝነቱ ወደ ሌላ አመት እንዲሻገር ይፈልጋሉ።

በእንግሊዝ ውስጥ በኤፍ ኤ ካፕ እንዲሁም በካራባዋ ካፑ የቪዲዬ ዳኝነት ከነ ችግሩም ቢሆን አገልግሎት ላይ መዋሉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የፕሪሚየር ሊጉ ሀላፊዋች የVAR ቴክኖሎጂውን በፕሪሚየር ሊጉም ሊጠቀሙ እንደሆነ ገልፀዋል።

የፕሪሚየር ሊጉ ቃል አቀባይ በሰጡት አስተያይትም ፦ “ያለ ምንም ችግር የዳኝነት ሂደቱን ሊያግዝ የሚችል አዲሱን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ዝግጁ ነን፤ የቪዲዬ ዳኝነት ሲስተሙን በሌሎች ውድድሮችም ላይ እንደተጠቀምነው በፕሪሚየር ሊጉም ለመጠቀም ዝግጁ ነን.” እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር አፕሪል 13 ላይ ሁሉም የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የቪዲዬ ረዳት ዳኝነቱ ስራ ላይ ይዋል ወይስ ይዘገይ የሚለውን ምርጫ የሚያደርጉ ሲሆን ከ20ዋቹ ክለቦች ውስጥ 14ቱ ስራ ላይ ይዋል ብለው ድምፅ ከሰጡ በያዝነው የውድድር አመት አገልግሎት ላይ የሚውል ይሆናል።

ነገር ግን ስራ ላይ ይዋል የሚለው ድምፅ ከ14 በታች ከሆነ ሲስተሙ ወደ ቀጣይ አመት ማለትም 2019/2020 የውድድር አመት የሚዘዋወር ታውቋል፤ ይህንኑ የቪዲዬ ዳኝነት ቴክኖሎጂ በሩሲያው የአለም ዋንጫም አገልግሎት ላይ የሚውል ይሆናል።

Advertisements