“በግራ ተከላካይነትም ቢሆን እንኳ ልጫወት እችላለሁ።” – ሃዛርድ

ኤዲን ሃዛርድ የቼልሲው አስልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ እንዲጫወት ባዘዙት በየትኛውም ቦታ ላይ ቢጫወት ደስተኛ እንደሚሆን ተናግሯል።

ሃዛርድ በዚህ የውድድር ዘመን ከዚህ ቀደም ይጫወትበት ከነበረው የፊት ለፊት የክንፍ ተጫዋችነት ሚና በእጅጉ በተለየ ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ሃሰተኛ 9 ቁጥር ሚና ተሰጦት ሲጫወት ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ዘገባዎች እደሚያመለክቱት መረጃዎች ከሆነ ግን ተጫዋቹ ይህ ቦታ ምቾት አልሰጠውም። ነገር ግን በብሄራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው ተጫዋቹ ግን በዚህ አይስማማም።

“እኔ የምፈልገው ወደሜዳ መግባት ነው። 9 ቁጥር፣ 10 ቁጥር ወይም አሰልጣኙ በሚፈልገው በግራ ተከላካይነትም ቢሆን እንኳ ልጫወት እችላለሁ። በዚህ ችግር የለብኝም። ሁልጊዜም እንደማደርገው ያለኝን ነገር ሁሉ እሰጣለሁ።” ሲል ሃዛርድ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኙ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ተጫዋቹን በማይፈልገው ሚና ላይ እንደማይጠቀሙት በተናገሩበት ከብሄራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ሆኖ ተነግሯል።

በተያያዘም በመጪው ክረምት ስታምፎርድ ብሪጅን ለቆ እንደባርሴሎና ወዳሉ ክለቦች እንደሚዛወር ወሬዎች የሚናፈሱበት ሃዛርድ ስለመጪ ጊዜው ከመናገር ተቆጥቧል።

“በቼልሲ ደስተኛ ነኝ።” ሲል ተናግሮ “ስለውድድር ዘመኑ መጨረሻ እያስበኩ እገኛለሁ። በኮንትራቴ ላይም ሁለት ቀሪ ዓመታቶች አሉ።” በማለት ገልፅዋል።

የ27 ዓመቱ ቤልጂየማዊ ተጫዋች በዚህ የውድድር ዘመን ለሰማያዊዎቹ 41 ጊዜ የተጫወተ ሲሆን በእነዚህ ጨዋታዎች ላይም 15 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ 11 ግብ መሆን የቻሉ ዕድሎችን ደግሞ ማመቻቸት ችሏል።

ተጫዋቹ ዛሬ (ማክሰኞ) ሃገሩ ከሳኡዲ አረቢያ ጋር በምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ የሚሰለፍ ከሆነ ለሃገሩ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች 83 ያደርሳል።

Advertisements