“ኩቲንሆም እንደ ኔማር ሁሉ ምርጥ ነው” – ዳኒ አልቬዝ

Image result for coutinho brazil

 

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

ዳኒ አልቬዝ የኔማር በጉዳት ምክንያት ከብራዚል ቡድን ውጭ መሆኑ እንደማያሳስበው እና በኩቲንሆ ላይ እምነቱ እንዳለው ገለፀ።

ብራዚል ወደ ሩሲያው የአለም ዋንጫ ለመጓዝ በጉዳት ምክንያት ያጣችውን ኮከቧን ኔማርን ከጉዳት መመለስ እየጠበቀች ቢሆንም ተከላካዬ ዳኒ አልቬዝ እንዲሁ የቡድኑ አሰልጣኝ ቲቴ የኔማር ከቡድኑ ውጭ መሆን እንደማያሳስባቸው ገልፀዋል።

አሰልጣኙ ቲቴ እንዲሁም ዳኒ አልቬዝ ከጋዜጠኞች ጋር ብደረጉት ቆይታ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል፡ ዳኒ አልቬዝ – ” እኔ እንደማስበው ኩቲንሆ ኔማር ባለበት ደረጃ የሚገኝ ተጨዋች ነው፤ በሁሉም ጨዋታዋች ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ይፈጥራል በብሄራዊይ ቡድኑ ጨምሮ፤ ከእንደሱ አይነት ተጨዋች ጋር መጫወት ያስደስታል።”

ቲቴ በሰጠው አስተያየትም – ” ለአንድ ተጨዋች ምን አይነት አስፈላጊ ነገሮች አሉ ብላችሁ ብትጠይቁኝ? ኩቲንሆ ሁሉም አለው. ” ኩቲንሆ የሚሰራው ነገር ሁሉ በጣም ጠንካራ ነው, ኳስ ሲያቀብል, ተወዳዳሪነቱ እንዲሁም ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ሲቀብል እና አሁን በጥሩ ብስለት ላይ ነው ያለው።

” የቀድሞው የሊቨርፑሉ እና የአሁኑ የባርሴሎና ሚድፊልደር ፊሊፔ ኩቲንሆ አለም ላይ ካሉ ምር ጥ አማካኞች ውስጥ አንዱ ቢሆንም ብራዚል ባዘጋጀችው 2014ቱ የአለም ዋንጫ ማሳተፍ ሳይችል ቀርቷል፤ በሩሲያው የአለም ዋንጫ ላይ ሀገሩን ከወከለ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።

Advertisements