ፍቺ / ፋቢዮ ካፔሎ እና ጂያንግሱ ሰኒንግ ተለያዩ

​የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት ፋቢዮ ካፔሎ ከቻይናው ጂያንግሱ ሰኒንግ አሰልጣኝነታቸው በጋራ ስምምነት ተለያዩ።

ስካይ ኢታሊያን ጨምሮ ሌሎች የቻይና መገናኛ ብዙሀን በሰፋት እንዳስተጋቡት ከሆነ በሰኔ 2017 ላይ የቻይናውን ቡድን እንዲያሰለጥኑ የተቀጠሩት ፋቢዮ ካፔሎ ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል።

በቻይና ሱፐርሊግ ጂያንግሱ ሰኒንግን ይዘው አጀማመራቸው ያላማረው ካፔሎ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ብቻ በመያዝ 12ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ደካማ አጀማመር አድርገዋል።

ዘገባዎች እንደሚያስረዱት ከሆነ ካፔሎ ከሀላፊነታቸው የለቀቁት ከክለቡ አመራሮች ጋር ባለመስማማታቸው እንጂ በደካማ አጀማመራቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ካፔሎ ቻይናን ለቀው አሰልጣኝ ወደሚፈልገው የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን በማቅናት ጂያን ፒሮ ቪንቹራን የመተካት እድል እንዳላቸው እየተነገረ ይገኛል።

በጣሊያን ብሔራዊ ቡድንም አሰልጣኝ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት ሮቤርቶ ማንቺኒ፣አንቶኒዮ ኮንቴ፣ክላውዲዮ ራኒየሪ እና ካርሎ አንቼሎቲ ጋር ጠንካራ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው ይጠበቃል።

ጣሊያን ባለፈው ህዳር ወር ላይ ከአለም ዋንጫ ተሳትፎ ውጪ ከሆነች በኋላ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጂያን ፒሮ ቬንቹራን አሰናብታ በምታካቸው ለጊዜው ከ 21 አመት በታች የሚያሰለጥኑት በልዊጂ ዲባጂዮ እየሰለጠነች እንደሚገኝ ይታወሳል።

 

Advertisements