አርሴን ዌንገር ከአርሰናል ሀላፊነታቸው በኋላ ምን ለመስራት አስበዋል?

ከአርሰናል ጋር ጥብቅ ግኑኝነት ያላቸው አርሰን ቬንገር ከ 22 አመት ቆይታ በኋላ ከመድፈኞቹ ጋር ለመለያየት መቃረባቸው እየተነገረ ባለበት ወቅት ከቡድኑ ጋር ቢለያዩ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ባለ ትሉቁን ጆሮ የቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫን 2006 ላይ ለማንሳት ቢቃረቡም ባርሴሎና ከኋላ በመነሳት ዋንጫውን በመንጠቅ ሊያሳኩት በተቃረቡት ህልማቸው ላይ ውሀ አፍሶበታል።

ቬንገር በአርሰናል ቆይታቸው በሜዳ ውስጥና ውጪ ስማቸው በጉልህ ይነሳል። ከመድፈኞቹ ጋር በቻምፕየንስ ሊጉ ማሳካት ካልቻሉበት ውጪ ታላላቅ ዋንጫዎችን አሸንፈዋል።

የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫም ካነሱ 14 አመት የሞላው ሲሆን በቅርቡ ደግሞ ወደ ቻምፕየንስ ሊጉ ለማለፍ እየተቸገሩ ይገኛሉ።

ቬንገር እንደ ቀድሞውኑ በደጋፊዎች እምነት ማግኘት ባለመቻላቸው ከክለቡ እንዲለቁ የሚሰሙ ድምፆች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ይህም የደጋፊዎች ተቃውሞ አሰልጣኙ የአንድ አመት ኮንትራት እየቀራቸው በክረምቱ ከቡድኑ ጋር የመለያየት እድላቸው ያሰፋው ሆኗል።

ከአርሰናል ጋር ቢለያዩ በቀጣዩ ምን ሊሰሩ እንደሚችሉ የተጠየቁት ቬንገር ከእግርኳስ ሙሉለሙሉ መለየት እንደሚከብዳቸው ተናግረዋል።

በአሰልጣኝነት መቆየት እንደሚፈልጉ የተጠየቁት ቬንገር “በአካል ብቃቴ ላይ ጠንካራ እስከሆንኩኝ እና ፍላጎት እስካለኝ ድረስ እያሰለጠንኩኝ መቆየት እፈልጋለው።”ሲሉ ሌላ ቡድን ሊያሰለጥኑ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል።

Advertisements