“አርጀንቲናዊያን ፈጣሪያቸውን ሊያመሰግኑት ይገባል መሲን ሰጥቷቸዋል”  – ዲያጎ ኮስታ

Image result for messi

 

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

ስፔናዊዬ እና የአትሌቲኮ ማድሪድ አጥቂ የሆነው ዲያጎ ኮስታ ሀገሩ ስፔን አርጀንቲናን 6 ለ 1 በረመረመችበት ጨዋታ ላይ አርጀንቲናዊያን ፈጣሪ ሜሲን ስለሰጣቸው ፈጣሪያቸውን ሊያመሰግኑት ይገባል ሲል ተናገረ።

በሀገራት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ አርጀንቲናን በአትሌቲኮ ማድሪድ ሜዳ የጋበዘችው ስፔን ምትሀተኛው ኮከቧን ሊዬኔል ሜሲን በጉዳት ምክንያት ያላሰለፈችውን አርጀንቲናን 6 ለ 1 ስታሸንፍ ዲያጎ ኮስታ 1 ጎል በስሙ ማስመዝገብ ችሏል። ከትላንቱ ምሽት በሆላ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ የራቀው እና ለሀገሩ ምንም ነገር አልሰራም እየተባለ ለሚተቸው ሊዬኔል ሜሲ ለቡድኑ ምን ያህል አሰፈላጊ ተጨዋች እንደሆነ የታየበት ነው ይላል ኮስታ።

” አርጀንቲናዊያን ሜሲን በጣም ይተቹታል፤ ነገር ግን ሜሲ በማይኖርበት ጊዜ ሌላ ናቸው ይህንን ልትነግሯቸው ይገባል።” ” እንደሜሲ አይነይ ተጨዋች ሊተች አይገባውም ፤ እንደውም እሱ ስላላቸውን ፈጣሪን ሊያመሰግኑ ይገባል፤ ከሀገሩ ጋር መጥፎ ጨዋታ ቢጫወት እንኳን ሁሌም ሜሲን በደንብ ተንከባክቦ መያዝ ይገባል፤ እሱ ሜዳ ውስጥ ስላለ ብቻ ልዬነት መፍጠር ይችላል።”

ዲያጎ ኮስታ አርጀንቲና ወደ ሩሲያው የአለም ዋንጫ ለማለፍ አጣብቂኝ ውስጥ በገባችበት ስአት በሊዬኒል ሜሲ ሀትሪክ ወደ አለም ዋንጫው ማለፏ መቻሏ የሚታወስ ነው።

Advertisements