እምነት ክህደት / ኒውካስትል በመለያው ላይ ካለው ማስታወቂያ ጋር በተያያዘ በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የቀረበበትን ክስ አመነ

ኒውካስትል ዩናይትድ ከ 18 አመት በታች ቡድኑ የማሊያ ማስታወቂያ ጋር በተያያዘ በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የቀረበበትን ክስ አምኗል።

የቀድሞው ጠንካራ የፕሪምየር ሊጉ ተፎካካሪ ክለብ “ፈን 88” የተሰኘ ምልክትን ወጣት ቡድኑ በሚጠበቀምበት ማለያ ላይ በመለጠፉ የእግር ኳስ ማህበሩን ደንብ የጣሰ ጥፋት መፈፀሙ ታውቋል።

ማህበሩ ከመለያ ማስታወቂያ ጋር በተያያዘ ባለው ህገ ደንብ ላይ ከ 18 አመት በታች ቡድኖች በሚለብሱት ማሊያ ላይ የአልኮልና የቁማር ነክ አገልግሎትና ተግባራት የሚያከናውኑ ድርጅቶች ማስታወቂያ እንዳይለጠፍ ያዛል።  

ነገርግን መቀመጫውን በቻይና ያደረገው “ፈን88” የተሰኘው ተቋም የቀድሞውን የኒውካስትል የማሊያ አጋር “ዎንጋን” በመተካት ባሳለፍነው ክረምት በስምንት ሚሊዮን ፓውንድ አመታዊ ክፍያ የክለቡ የማሊያ ስፖንሰር ሆኖ መፈራረሙ ኒውካስትልን ለክስ ዳርጎታል።

የቻይናው “ፈን88” የገቢ ምንጩ በኢንተርኔት ከሚገኝ የአቋማሪነት ተግባራት ጋር የተያያዘ መሆኑ በዘገባው ተያይዞ ተጠቅሷል።

Advertisements