“በዚህ አመት ብቻ ሳይሆን በየአመቱ የወርቅ ጓንቱን ማሸነፍ እፈልጋለው” – ዴቪድ ዴህያ

Image result for david de gea

ዴቪድ ዴህያ ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

ስፔናዊዬ  ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴህያ የወርቅ ጓንቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ማሸነፍ እንደሚፈልግ ገለፅ። በያዝነው ሲዝን ካለፉት ጊዜያት በበለጠ በማንችስተር ቤት ድንቅ አቋሙን በማሳየት ላይ የሚገኘው እና ከአለማችን ቁጥር አንድነቱን ይበልጥ ለማስመስከር እየለፋ የሚገኘው ዴህያ የወርቅ ጓንቱን መሽነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

በክለቡም ይሁን በሀገሩ የመጀመሪያ ተሰላፊነት ያገኘው ዴህያ በያዝነው የውድድር ዘመን በማንችስተር ማሊያ በ15 ጨዋታዋች ምንም ጎል ሳይቆጠርበት መውጣት ችሏል፤ ከዚህ በፊት ጆ ኸርት በ18 ጨዋታዋች ምንም ጎል ሳይቆጠርበት በመውጣት የወርቅ ጓንቱን መሽነፍ ችሏል። ዴቪድ በሰጠው ሀሳብም ፦

” በዚህ አመት ብቻ ሳይሆን በየአመቱ የወርቅ ጓንቱን መሽነፍ እፈልጋለው ” ” እንደዚህ አይነት ሽልማቶችን ስታሸንፍ ያንተ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ቡድኑ በመከላከሉ ላይ የሰራው ስራ ጠንካራ እንደሆነ ያሳያል፤ በዚህ ሲዝን በደንብ መከላከል ችለናል” ዴህያ በፕሪሚየር ሊጉ ከዴህያ በመቀጠር ኤደርሰን 14 ፤ ቲቦ ኮርቱዋ 13 ጨዋታዋች ላይ ጎላቸውን ሳያስደፍሩ መውጣት ችለዋል፤

ዴህያ ከ2015 ጀምሮ በሪያል ማድሪድ በጥብቅ ሲፈለግ የነበረ ቢሆንም በትንሽ ችግር ምክንያት ዝውውሩ ሳይሳካ መቅረት ችሏል። ዴህያ እያሳየው ባለው ምርጥ አቋም ምክንያት ጆዜ ለማንችስተር ባለስልጣናት በምንም አይነት ዋጋ መሸጥ እንደሌለባቸው አሳውቀዋል።

Advertisements