ፊፉ እንግሊዛዊያን ዳኞችን በአለም ዋንጫው ሳያካትት ቀረ

ፊፋ በ 2018 የአለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ 99 ዳኞችን ይፋ ሲያደርግ አንድም እንግሊዛዊ በዝርዝር ውስጥ ሳያካትት ቀርቷል።

ሊጀመር ጥቂት ወራት ብቻ በቀሩት የ 2018 የራሺያዊ የአለም ዋንጫ ላይ የሚያጫውቱት ዳኞች ተለይተው ታውቀዋል።

ፊፋ 99 ዳኞች እና ረዳት ዳኞችን ከተለያዩ ሀገራት ሲመርጥ የእንግሊዛዊያን ዳኞች ስም አለመካተቱ በእንግሊዛዊያን ዳኞች ላይ ያለው የዳኝነት ችግር አጉሉቶታል።

ጠንካራ ፉክክር በሚደረግበት የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ የሚያጫውቱ ዳኞች ውስጥ የነበሩት ማርክ ክላተንበርግ እና ሀዋርድ ዌብ ይጠቀሳሉ።

ሁለቱ ዳኞች ስራቸውን በማቆማቸው እንግሊዛዊያን በአለም ዋንጫው በብሔራዊ ቡድናቸው ብቻ መወከላቸው እርግጥ ሆኗል።

ሀዋርድ ዌብ በ 2010 እና 2014 ላይ እንግሊዝን ወክለው በአለም ዋንጫው ላይ የተሳተፉ ሲሆን ስፔን እና ሆላንድ አድርገውት የነበሩትን የፍፃሜ ጨዋታ መምራትም ችለው ነበር።

በተያየዘ ዜና ኢትዮጵያን በመወከል ኢንተርናሽናል አልቢተር በአምላክ ተሰማ በአለም ዋንጫው ላይ ከሚሳተፉ ውስጥ ተካቷል።

Advertisements