“በዩናይትድ መጫወት የምፈልገው እንደ ወቅቱ የፔፕ ጓርዲዮላው ሲቲ ነበር” -ልዊ ቫንሀል

2014 ላይ ዴቪድ ሞይስን በመተካት ወደ ኦልድትራፎርድ ያቀኑት ልዊ ቫንሀል ቀያይ ሰይጣኖቹ እንዲጫወቱላቸው የሚፈልጉት ልክ እንደ ወቅቱ የፔፕ ጓርዲዮላው ማን ሲቲ እንደነበር ተናገሩ።

የሆላንድ ብሄራዊ ቡድንን ይዘው በአለም ዋንጫ ላይ የሶስተኛ ደረጃን ካሳኩ በኋላ ወደ ማንችስተር ያቀኑት ቫንሀል ከኦልድትራፎርዱ ክለብ ጋር ውጤታማ ጊዜን አላሳለፉም።

ከዋንጫ ፉክክር ርቀው የነበሩት ቫንሀል ፍልስፍናቸውን ጊዜ እንደሚያስፈልገው እና በሂደት የሚሻሻል እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቢቆዩም ቆይታቸው ብዙም ሳይረዝም ከክለቡ ሀላፊነታቸው ተነስተዋል።

በተለይ የማያጠቃው ኳስ በማንሸራሸር ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገው ቡድናቸው ለትችት ሁሉ ተጋልጦ እንደነበር ይታወሳል።

ቫንሀል በእንግሊዝ የነበራቸውን ቆይታ እንደ የወቅቱ ማን ሲቲ ለመጫወት ይፈልጉ እንደነበር ተናግረዋል።

“ለኔ ፔፕ ጓርዲዮላ የወቅቱ የፕሪምየርሊጉ ምርጥ አሰልጣኝ ነው።ፔፕ ሲቲን እንደ ማሽን አድርጎታል።እሱ እኔ በዩናይትድ መጫወት የምፈልገውን አይነት አጨዋወት እየተጫወተ ነው።ነገርግን እሱ ጥሩ ተጫዋቾች አሉት

“ለኔ የፍልስፍናዬ ሂደት ጊዜ የሚፈልግ ነበር፣ያለመታደል ሆኖ ከዩናይትድ ጋር ጊዜ አልተሰጠኝም።” ሲሉ ተናግረዋል።

Advertisements