ባትሹአዪ በዘረኝነት ጉዳይ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበርን ተቸ

የቦሩሲያ ዶርትሙንዱ የፊት ተጫዋች ሚቺ ባትሹአዪ ከአታላንታ ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ የደረሰበትን የዘረኝነት ክስ ውድቅ ያደረገውን የአውሮፓ እግርኳስ ማህበርን በማህበራዊ ሚዲያው ወርፏል።

በጀርመኑ ክለብ በውሰት የቆይታ ጊዜ ላይ የሚገኘው የቼልሲ አጥቂ ቦሩሲያ ዶርቱትሙንድ ከጣሊያኑ ክለብ ጋር ባደረገው የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ላይ በደረሰበት የዘረኝነት ጥቃት ክስ አቅርቦ የነበረ ሲሆን የአውሮፓ እግርኳስ ማህበርም ክሱን ተቀብሎ እንደሚመለከት ገልፃ ነበር።

ይሁን እንጂ የእግርኳስ ማህበሩ በትናንትናው ዕለት (ሐሙስ) ተጨማሪ ምርመራ ማድረጉን እንደማይቀጥል ገልፅዋል። ይህን ተከትሎም ባትሹአዪ በግል የትዊተር ገፁ የተሰማውን ስሜት “በምናቤ መሆን አለበት።” እንዲሁም “‘ተራ የዝንጀሮ ድምፅ ብቻ ነው።’- የ2018ቱ ሰው።” ሲል በሹፈት ገልፅዋል።

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ክሱን ምርመራውን ማቋረጡን እንጂ ለምን ምርመራውን ለማቋረጥ እንደወሰነ አልገለፀም።

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በመጋቢት ወር የሊቨርፑሉ ወጣት ተጫዋች ርሂያን ብሬውስተር በአውሮፓ ወጣቶች ሊግ ጨዋታ ላይ በስፓርታ ሞስኮ ደጋፊዎች የደረሰበትን የዘረኝነት ክስ አቤቱታ ውድቅ ካደርገ ወዲህ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ውድቅ ያደረገው የዘረኝነት ክስ ይሆናል።

ቤልጂየማዊው ተጫዋች በስታንፎርድ ብሪጅ ስኬታማ ጊዜን ማሳለፍ ሳይችል ቀርቶ በጥር ወር ወደዶርትሙንድ በውሰት በማምራት በፍጥነት የቡንደስሊጋውን ህይወት መላመድ ችሏል። የ24 ዓመቱ አጥቂ ለዶርትሙንድ እስከሁን ባደረጋቸው 11 ጨዋታዎች ዘጠኝ ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

Advertisements